በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ ጥናትና ዲዛይን ሥራዎችን ማከናወን ለግንባታ ጥራትና የውሃ ተቋማትን በዘላቂነት ለማስተዳደር የሚያግዝ መሆኑን ተገለፀ ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ የአምስት አነስተኛና መካከለኛ ከተሞች በክልሉ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት አማካሪነት የተጠናው የመጠጥ ውሀ የአዋጭነት ጥናትና ዲዛይን ድራፍት ዶክመንት ግምገማ በወልቂጤ ከተማ ተካሄዷል ።
የክልሉ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ እንደተናገሩት በክልሉ በሚገኙ መካከለኛና አነስተኛ ከተሞች ያለውን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ለመፍታት በአማካሪ ድርጅቱ የቀረበውን የጥናትና ዲዛይን ድራፍት ሰነድ ዙሪያ የተሰጠውን ግብአት በማደራጀት ተገቢው ሊፈፀም ይገባል ብለዋል።
በከተሞቹ የህዝብ ብዛትና ተያያዥ የሆኑ መረጃዎች አስተማማኝ ደረጃና ተቀባይነት ባለው አግባብ እንዲደራጅ በህዝብና ቤት ቆጠራ መስሪያ ቤት እና በክልላችን ፕላን ልማት ቢሮ በሚገኙ መረጃዎች ላይ የተመሰረተ መሆኑ እንደሚገባ አቶ ዳዊት አመላክተዋል።
ምክንያቱም በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ ጥናትና ዲዛይን ሥራዎች ማከናወን ለግንባታ ጥራትና የውሃ ተቋማትን በዘላቂነት ለማስተዳደር የሚያግዝ መሆኑን የቢሮ ኃላፊ ገልፀዋል።
በሌላ በኩል የውሀ መገኛ ቦታዎችና ምንጮች በተመለከተ የጥናትና ዲዛይን ስራው በዋናነት በአካባቢው ታሸገው የተቀመጡ ጉድጓዶችን እንዲሁም የሀገር ውስጥ ግብአቶችን የመጠቀም ብሎም የተለያዩ አማራጭ የሀይል አቅርቦት ላይ መመስረት ይገባል ብለዋል ።
የቢሮው ምክትል ሃላፊና የመጠጥ ውሃ ጥናትና ዲዛይን አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ኢ/ር አየለ ኬርጋ በክልሉ እየተገነቡ ያሉ የመጠጥ ውሀ ፕሮጀክቶች ላይ የክልሉ ዲዛይን፣ ግንባታ እና ቁጥጥር ድርጅት የላቀ ተሳትፎ እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ይህ ጥናት ተጠናቆ ወደ ተግባር ሲገባ ከ309 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተናግረዋል።
በድራፍት ጥናቱ ላይ የቀረበው የዋጋ ጥናት አቅምንና ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ሊታይ እንደሚገባ ምክትል ቢሮ ሃላፊው አመላክተዋል ።
የክልሉ ዲዛይን፣ ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር እስማኤል ወራቄ በበኩላቸው በቀረበው ድራፍት አስመልክቶ መድረኩ የተሰጡ ግብአቶችን በመውሰድ ከቀሪ ስራዎች ጋር በማስተሳሰር በትኩረት ይሰራል ብለዋል ።
ከቢሮው ጋር የተጀመሩ ቅንጅታዊ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘው ተናግረዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በከተሞቹ የሚስተዋለውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚያስችል የጥናት ድራፍት መቅረቡን አመላክተዋል።
በመድረኩ የተሰጡ ግብአቶችና አስተያየቶች በሶስት ቲም ተደራጅቶ ጥናቱ ይበልጥ ውጤታማ ማድረግ በሚያስችል አግባብ የፁሑፍ ግብአት ተደራጅቶ እንዲቀርብ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
በመድረኩ በአምስት አነስተኛና መለስተኛ ከተሞች በድራፍት ደረጃ የተዘጋጁ የጥናትና ዲዛይን ሰነዶች ቀርበው ተገምግሟል ።
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 