Skip to main content

የቢሮው ሥልጣንና ተግባር

ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት አሉት

የክልሉን የውሃ ሀብት ያስተዳድራል፣

የክልሉን የከርሰ ምድርና ገፀ ምድር ውሃ ሀብት በመጠንና በጥራት ይለያል፣ ጥቅም ላይ የሚውልበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣

የውሃ ልማትና አስተዳደር ማኑዋሎችንና ደረጃዎችን ያዘጋጃል እንዲሁም ሌሎች የውሃ ሴክተር ስራዎችን ይቆጣጠራል፣

የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ዝርዝር ጥናት ያጠናል፣ ግንባታዎችን ያከናውናል፣

የከተማና ገጠር የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን እንዲያድግ ያደርጋል፣ ደረጃውን ይወስናል፣ የቴክኒካዊ ሥራዎችን አፈፃፀም ይከታተላል፣

የገጠር መጠጥ ውሃ ተቋማት አስተዳደር ኮሚቴዎችን ያደራጃል ሕጋዊ የሰውነት ፈቃድ ይሰጣል፣ የከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅቶችን ያደራጃል፣

በክልሉ የውሃ ተፋሰሶች ፍትሐዊና ሚዛናዊ የውሃ ክፍፍልና ምደባ መኖሩን ይቆጣጠራል፤

የውሃ ዕጥረት ባለባቸው የክልሉ አካባቢዎች የአስቸኳይ ጊዜ የውሃ አቅርቦት ያመቻቻል፣ ችግሩንም በዘለቄታዊነት ለማስወገድ የሚያስችሉ ተግባራትን ያከናውናል፣

የውሃ አካላት ብክለትን ይከላከላል፣ ይቆጣጠራል፣ የውሃ ናሙና ይሰበስባል፣ የላብራቶሪ ምርመራ ያደርጋል፣

 በውሃና በመስኖ ልማት ስራ ለሚሰማሩ ተቋራጮች፣ አማካሪዎችና ባለሞያዎች ደረጃቸውን ይወስናል፣ የሥራ ፈቃድ ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል፣

 የክልሉን የመስኖ ልማት ሽፋን ለማሳደግ የመስኖ ልማትና የማጠንፈፍ ሥራዎች ጥናትና ዲዛይን ያከናውናል፣ የግንባታ ጨረታ ያዘጋጃል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣

 የወንዞች ፍሰት አቅጣጫ መግራት እና የጐርፍ መከላከያ ሥራዎች ጥናት ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ሥራዎችን ያከናውናል፣

 በክልሉ የሚካሄዱ የመስኖ ኮንስትራክሽን ሥራዎች መስፈርት ያዘጋጃል፣ ተግባራዊነቱን ይመራል፣

 የመስኖ አለኝታ ጥናት፣ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ይመራል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣ አቅም ይገነባል፣

 የመስኖ ተቋማትን ይንከባከባል፣ ይጠግናል፣ የመስኖ ተቋሞችን በአካባቢው ሙያተኞችን በማሰልጠን እንዲንከባከቡና እንዲያስተዳድሩ ያበቃል፣

 የክልሉ የማዕድን ሀብት አለኝታ ጥናት ያደርጋል፣ በልማት ላይ እንድውል አቅጣጫ ያስቀምጣል፣ በበላይነት ያስተዳድራል፤

 የማዕድን ልማቶችን የአከባቢን እና የህብረተስብ ደህንነት በጠበቀና ተጠቃሚነቱን በሚያረጋግጥ መልኩ መፈጸሙን ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ያረጋግጣል፣ ይከታተላል፣

 አማራጭ የኢነርጅ ተክኖሎጅዎችን ያለማል ፣ያስፋፋል ፣ ያሰራጫል፤

 አነስተኛ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመነጨት የሚችሉ ወንዞችን ከሚመለከተው አካል ጋር ያጠናል፣ስፈቀድም ጥቅም ላይ እንድውል ያደርጋል፤

ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡