የመጠጥ ውሃ ግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ዳሬክቶሬት
የመጠጥ ውሀ ግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት
የመጠጥ ውሀ ግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ማለት የመንግስት የልማት እቅድ፣ የመጠጥ ውሀ አቅርቦት ጥያቄ እና የመጠጥ ውሃ ሽፋን እንደ ግብዓት ተቀብሎ እንዲሁም የመጠጥ ውሃ ፍላጎት ለማሟላት የተዘጋጁ የጥናትና ዲዛይንና ዶክሜንቶችን ከጥናትና ዲዛይን በመውሰድ የመጠጥ ውሃ ተቋማት አቅርቦት ግንባታ ክትትልና ቁጥጥር በማጠናከር፣ አዳዲስና ነባር የገጠርና የከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የግንባታ ስራዎች በማጠናቀቅ ተደራሸ በማድረግ፣ የከተሞችና የገጠር መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክቶች ከኮንትራክተሮች ጋር ዉል በመግባት፣ የሙያ ድጋፍ በማድረግ፣ ተቋማት በዲዛይናቸዉ መሰረት ስለመሰራታቸዉ ክትትል በማድረግ፤ አገልግሎት ለማይሰጡ የመጠጥ ዉሃ ተቋማት የጥገና ግንባታ በማድረግና በማጠናቀቅ ተገልጋዩን ህብረተሰብ በንቃት በማሳተፍ የመጠጥ ውሃ ተቋማትን የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን በማከናወን ለክልሉ ህዝብ ደረጃውን የጠበቀ በቂና አስተማማኝ የንፁህ መጠጥ ውሀ የማቅረብ ስራ ይሰራል፡፡
የዳይሬክቶሬቱ ዋና ዋና ተግባራት
ተጠንቶ የተዘገጁ የመጠጥ ውሃ ሰነዶችን መለየት
በተጠናው ሰነድ መሠረት ዕቅድ ዝግጅት ማድረግ
ለግንባታ የሚሆን የጨረታ ሰነዶችን በማዘጋጀት ተደራሽ ማድረግ፣
የጨረታ ግምገማን እና የውል ዝግጅት አፈፃፀም በመገምገም ማስተዳደር
የግንባታ/ቁፋሮ ቦታ ለስራ ተቋራጭ/አማካሪ የማስረከብ አገልግሎት፣
ተጠቃሚውን ህብረተሰብ በማንቀሳቀስ በግንባታው ወቅት እንዲሳተፉ ምክር የመስጠት ፣
የግንባታ/ቁፋሮ ስራዎችን በራስ ኃይልና outsource የማድረግ አገልግሎት፣
የውሀ ተቋምን ግንባታ ሲጠናቀቅ ፈትሾ የማረካከብ አገልግሎት፤የተገነባውን ተቋም ለሚያስተዳድረው አካል የማስረከብ አገልግሎት፣
የተጠናቀቁ /በሂደት ላይ የሚገኙ የግንባታ/የቁፋሮ ፕሮጀክቶችን መረጃ ያደራጃል፣ለሚመለከታቸው ክፍሎች ያስተላልፋል፣
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 