ራዕይ ተልዕኮና እሴት
ተልዕኮ
ህብረተሰቡንና ሌሎች የልማት ሀይሎችንና አጋሮችን በማስተባበር ፖሊሲዎችን ፣ ስትራቴጂዎችንና ፕሮግራሞችን መሠረት ያደረገና ተፈፃሚነት ያለው የልማት መርሃ ግብር በመቅረጽ የተቀናጀ እና ዘለቄታዊ የማዕድንና ኢነርጂ አስተዳደር ማስፈንና ሀብታችንን ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ ህዝብ ዕድገትና ብልፅግና ወሳኝ ሚና መጫወት በሚችል መልኩ እንዲለማ ማድረግ፡፡
ራዕይ
በ2022 የማዕድንና የኢነርጂ ሀብቶቻችን በተቀናጀ ፣ በዘለቄታዊ ፣ ፍትሐዊና ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማስተዳደር እና ለማልማት የሚያስችሉ ህጋዊና ተቋማዊ አሰራሮች ጎልብተው የህብረተሰቡ የአማራጭ ኢነርጂ ተጠቃሚነት አድጎና የክልሉ እምቅ የማዕድን ሃብት በተገቢው ሁኔታ ለምቶ ለፈጣን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ ድርሻ አበርክቶ የክልሉ ህብረተሰብ ተጠቃሚ ሆኖ የተሻለ ሕይወት ሲመራ ማየት፡፡
እሴቶች
ለዘላቂና ለተቀናጀ ማዕድንና ኢነርጂ ሀብት ልማት ጠንክረን እንሰራለን፡፡
የማዕድንና ኢነርጂ ዘርፍ የመረጃ ባንክ ነን፡፡
ሴቶች የማዕድንና ኢነርጂ ልማት እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንደርጋለን፡፡
የማዕንና ኢነርጂ ልማት በሌሎች የልማት ዘርፎች ላይ ወሳኝ ደርሻ አላቸዉ፡፡
ለተጠቃሚው በቂና ዘላቂ የኢርጂ አቅርቦት እንሰጣለን፡፡
በህብረተሰብ ተሳትፎ የማዕድንና ኢነርጂ ሀብት ልማት ይረጋገጣል፡፡
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 