Skip to main content

የመጠጥ ውሃ /አቅ/ሳ/ ዘርፍ

የውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ የመጠጥ ውሃ  አቅርቦትና ሳኒቴሽን ዘርፍ ተግባርና ኃላፊነት

 

የመጠጥ ውሀ አቅርቦትና ሳኒቴሽን  ዘርፍ በመንግስት ካፒታልና ዘላቂ ልማት ፕሮግራም እንዲሁም በተለያዩ ፕሮግራሞችና ረጂ ድርጅቶች በወጪ መጋራት ስርዓት (Matching Fund) (አህዳዊ ዋሽ፣ ኮ-ዋሽ ፣ ባስኬት ፈንድና ዩኒሴፍ) የሚገነቡ የንፁህ መጠጥ ውሀ ግንባታ ፕሮጀክቶችን የቅርብ ክትትል፣ ድጋፍና ቁጥጥር በማድረግ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ  ደረጃውንና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ እንዲጠናቀቅ የሚያደርግ ዘርፍ ነው፡፡ ይህ ዘርፍ ለቢሮ የሚመደበውን ከፍተኛ የግንባታ በጀትና ሀብት ትልቅ ድርሻ ያለው ከመሆኑም በላይ በህብረተሰቡ ውስጥ የሚነሳውን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲሁም የንፁህ መጠጥ ውሀ ችግሮች ምላሽ የሚሰጥ ዘርፍ ነው፡፡ በዘርፉ ይህን ተልዕኮ እና ተግባር የሚወጣ የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት በስሩ እንዲደራጅ ያደርጋል፡፡ 

በተጨማሪም ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ብቁ የተደረጉ የንፁህ መጠጥ ውሀ ተቋማት ለህዝቡ ዘላቂ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የውሀ ኮሚቴዎችን የማደራጀት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች የመስጠት የውሀ ማህበራትና ፌደሬሽኖችን በማደረጀት የውሀ ተቋማት በብቃትና በኃላፊነት መንፈስ   የማስተዳደር  በተገቢው አግባብ ህብረሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ ሥራዎችን የሚሰራ ከመሆኑም በላይ የውሀ ተቋማት ከቅድመ ብልሽት  መከላከል ቀላል ብልሽት ፣ መካከለኛ ብልሽት እና ከባድ ብልሽት ሲገጥማቸው ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመቀናጀት ተገቢውን ጥገናና የመልሶ ግንባታ በማካሄድ ለአገልግሎት እንዲበቃ የማድረግ ሥራዎችን የሚሰራ ሲሆን ይህን ተልዕኮ እና ተግባር የሚወጣ የውሀ ተቋማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በስሩ እንዲደራጅ ያደርጋል፡፡