የባስኬት ፈንድ ፕሮግራም /Basket Fund Program
መግቢያ ከከተማንፁህየመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አቅርቦት አንጻር መንግስት በተናጥል የሚያከናውነው ስራ የታቀደውንግብለማሳካት የሚያስችል አቅም ውስን በመሆኑ የህብረተሰቡን፣ የተለያዩ የአጋር ድርጅቶችንና ተቋማትን አቅምበሰፊው መጠቀም የሚያስችል የማስፈጸሚያ እስትራቴጂ ነድፎ በመተግበርላይ ይገኛኛል በዚህ ረገድ የውሃ ልማት ፈንድ ጽ/ቤት ለከተሞች የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን እንዲሁም ለሰፋፊና መካከለኛ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ የሚውል ፋይናንስ ከፌደራል መንግስት ከውጭ አበዳሪና እርዳታ ሰጪ ተቋማትና አገሮች እያፈላለገ የህብረተሰቡን የመክፈል አቅም ባገናዘበ መልኩ ከውሃ ዘርፍ አስተዳደር ፖሊሲና ስትራቴጂ መርሆች አንዱ በሆነው ዋጋን በማስመለሰ መርህ(costrecoveryprinciple) ላይ በመመስረት ለተጠቃሚው ህብረተሰብ በረጅም ጊዜ እና በአነስተኛ ወለድ የሚከፈል ብድር ለመስጠት ታስቦ በጥር ወር1994 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር268/1994 የተቋቋመ መንግስታዊ ተቋም ነው፡፡
የፈንዱ ዋና ዓላማ ከላይ ከፍ ብሎ በተጠቀሰው መንገድ የሚያስተላልፋቸውን ብድሮች በስምምነቱ የጊዜ ማዕቀፍ ውስጥ መልሶ በመሰብሰብ ለሌሎች ተመሳሳይ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ጥያቄ ለሚያቀርቡ ከተሞች ፕሮጀችክቶች ማስፈፀሚያ የሚውል ተዘዋዋሪ ፈንድ ክምችት መፍጠርና ማስተዳደር ነው፡፡
የውሃ ልማት ፈንድ የሚያቀርበው ብድር በቂ የእፎይታ ጊዜ ያለውና ከ20 እስከ 30 ዓመት ጊዜ ውስጥ እጅግ አነስተኛ ከሆነ ወለድ (3%) ጋር ተመልሶ የሚከፈል ከትርፍ ይልቅ ልማቱ ላይ የሚያተኩር ሲሆን የአገራችንን ከተሞች የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ችግር በተቻለ ፍጥነት በመፍታት ከተሞቻችን በኢኮኖሚውም ሆነ በማህበራዊ እንቅስቃሴዎቻቸው ተወዳዳሪና ተፎካካሪ ሆነው ለነዋሪዎቻቸዉ ምቹ የመኖሪያ ሥፍራዎች እንዲሆኑ የሚተጋ ተቋም ሲሆን ከክልል እስከ ከተሞች ድረስ የሚገኙ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በብድር ሞዳሊቲው መሠረት ለፕሮጀክቶቹ የወጪ መጋራት በጀት (Matching Fund) በመመደብ ዓላማው የተሳካ እንዲሆን በቅንጅትና በትብብር መንፈስ በጋራ እየሰሩ ይገኛል፡፡
ከዚህ አንጻር የውሃ ልማት ፈንድ ጽ/ቤት በአንድ ቅርጫት ፈንድ ፕሮግራም ፋይናንስ (Basket Fund Program Financing) በኩል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ በ5 አነስተኛና መካከለኛ ከተሞች 253,300 ህዝብ (ሴት=129,183 እና ወንድ=124,117)ህብረተሰብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ የብድር ፋይናንሱ ምንጭ የልማት አጋሮች ከሆኑ የአለም ባንክ፣ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ፣ የፈረንሳይ እና የጣሊያን ልማት ድርጅቶች የተገኘ ሲሆን በመግባቢያ ሰነዱ መሰረት ለፕሮጀክቶቹ ማስፈጸሚያ ከተገመተው አጠቃላይ የኢንቨስትመንት ወጪ ውስጥ 57% በላይ የሚሆነው በውሃ ሀብት ልማት ፈንድ በኩል በረጅም ጊዜ እና በአነስተኛ ወለድ በሚከፈል ብድር በተገኘ ፋይናንስ የሚሸፈን ሲሆን ቀሪው 43% የሚሆነው ከክልል እስከ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ የመንግስት አስተዳደር ተቋማት በኩል በወጪ መጋራት መርህ (Matching Fund) የሚሸፈን ይሆናል፡፡
ከፕሮግራሙ አፈጻጸም ረገድ ባለፉት የትግበራ ዓመታት የቃዋ ቆቶ ከተማ ፤ ቡኢ ከተማ ፤ዳሎቻ ከተማ ፤ሺንሺቾ ከተማ መ/ው/ፕሮጀክት ግንባታ በማጠናቀቅ በድምሩ 187,030 ህዝብ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
ለከተሞችእና አከባቢው ዘላቂና አስተማማኝየንጹህ መጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን አገልግሎት እንዲቀርብ በማድረግ የህብረተሰቡን ጤና፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች እንዲሻሻል የሚደረገውን ጥረት ማገዝ ነው፡፡
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 