ተልዕኮ ራዕይና እሴት
የሴክተሩ ተልዕኮ፣ ራዕይና እሴት
ተልዕኮ
ህብረተሰቡንና ሌሎች የልማት ሀይሎችንና አጋሮችን በማስተባበር ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችንና ፕሮግራሞችን መሠረት ያደረገና ተፈፃሚነት ያለው የልማት መርሃ ግብር በመቅረጽ የተቀናጀ እና ዘለቄታዊ የውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ አስተዳደር ማስፈንና ሀብታችንን ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ ህዝብ ዕድገትና ብልፅግና ወሳኝ ሚና መጫወት በሚችል መልኩ እንዲለማ ማድረግ፡፡
በ2022 የውሃ፣ መስኖ፣ የማዕድንና የኢነርጂ ሀብቶቻችን በተቀናጀ፣ በዘለቄታዊ፣ ፍትሐዊና ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማስተዳደር እና ለማልማት የሚያስችሉ ህጋዊና ተቋማዊ አሰራሮች ጎልብተው በቂና አስተማማኝ ውሃና መስኖ በተፈላጊውን ጥራት ደረጃ ቀርቦ፣የህብረተሰቡ የአማራጭ ኢነርጂ ተጠቃሚነት አድጎና የክልሉ እምቅ የማዕድን ሃብት በተገቢው ሁኔታ ለምቶ ለፈጣን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ ድርሻ አበርክቶ የክልሉ ህብረተሰብ ተጠቃሚ ሆኖ የተሻለ ሕይወት ሲመራ ማየት፡፡
- ለዘላቂና ለተቀናጀ የውሃ፣መስኖ፣ማዕድንና ኢነርጂ ሀብት ልማት ጠንክረን እንሰራለን፡፡
- የውሃ፣መስኖ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ዘርፍ የመረጃ ባንክ ነን፡፡
- ሴቶች የውሃ፣መስኖ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንደርጋለን፡፡
- ውሃ ቁልፍ የልማት መግቢያ /Key entry point/ ነው፡፡
- የውሃና መስኖ ልማት በሌሎች የልማት ዘርፎች ላይ ወሳኝ ድርሻ አለው፡፡
- ለተጠቃሚው በቂና ዘላቂ የመስኖ ውሃ አቅርቦት እንሰጣለን፡፡
- ፍትሀዊ የመስኖ ተቋማት ስርጭት እናረጋግጣለን
- በህብረተሰብ ተሳትፎ የውሃ፣መስኖ፣ማዕድንና ኢነርጂ ሀብት ልማት ይረጋገጣል፡፡
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 