Skip to main content

የኤጀንሲው ሃላፊ መልዕክት

የኤጄንሲው ዋና ዳይሬክተር መልዕክት 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር

አቶ መኮንን መኔዶ ቀልቦሬ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማዕድንና ኢነርጂ ኤጄንሲ ከተቋቋመበት ከ2015 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ በክልሉ የሚገኙ እምቅ የማዕድንና ኢነርጂ ሀብቶችን በአግባቡ በመለየት እና በጥናት በማስደገፍ እንዲሁም በሌሎች የግል ባለሀብቶችና የሚመለከታቸው አካላት እንዲለሙ በማድረግ የማዕድኑ ዘርፍ በአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በተሰጠው ትኩረት መሰረት በተለይም የውጭ ምንዛሪ በማስገኘ፣ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚገቡ የማዕድናት ውጤቶችን እንዲሁም የማዕድን ኢንዱስትሪ ግብአቶችን በአገር ውስጥ በመተካት፤በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ለዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር የኢትዮጵያን የመጪዎቹ ዓመታት የብልፅግና ጉዞ የጎላ አስተዋፅኦ እንዲያበረክት እንዲሁም የአማራጭ ኢነርጂ ዘርፍ ከዋናው የሀይል መስመር ርቀው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ንጹህና አስተማማኝ የታዳሽ የኢነርጂ ምንጮችንና ቴክኖሎጂዎችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ዘርፉ ለገጠር ትራንፎርሜሽን ሊያበረክት የሚገባውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡

ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ ባለው መዋቅር በማዕድንና ኢነርጂ ዘርፎች የሚመነጩ፣ የሚሰበሰቡና የሚደራጁ የተለያዩ መረጃዎች ተዓማንነት ያላቸው እንዲሆኑ ከማድረግ አንጻር በባለፉት ዓመታት ከፍተኛ ርብርብ ሲደረግ የቆየና እምርታዊ ለውጥ ለማስመዝገብ የተቻለ ቢሆንም  አንዳንድ የጠራ መረጃ ከማደራጀትና ከማስተላለፍ፣ተቋማዊ መደበኛ  ተግባራትን በፕሮጀክት እሳቤ በጊዜ የለኝም መንፈስ ከመፈጸምና እያንዳንዱ መዋቅር በየመዋቅሩ መሬት ላይ ያሉ መረጃዎችን ቆጥሮ በመያዝ ወደ ውጤት ከመቀየር ፣ቀጣይነት ያለው ጠንካራ ድጋፋዊ ክትትል ከማድረግ ረገድ በቀጣይ ተወስዶ መሰራት ያለበት ነው፡፡

ይህንን ችግር ለመቅረፍ ዘመኑን የዋጀውን ዲጂታላይዜሽን ሲስተም በመጠቀም አስፈላጊውን መረጃ ለሚመለከተው አካል በተፈለገው ጥራትና ፍጥነት ለማድረስ በሴክተሩ አነሳሽነት እና በክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ቴክኒካል ድጋፍ የተከፈተው ዌብ ሳይት ሚና የሚጫወት በመሆኑ በክልሉ አቅም በዚህ ልክ በመሠራቱ ለተሳታፊ አካላት ከፍተኛ አድናቆት የሚቸረው ሲሆን ቴክኖሎጂው የምናስቀምጣቸውን መረጃዎችን ለዓለም የሚያስተዋውቅ በመሆኑ በዌብሳይቱ ላይ የሚላቀቁ መረጃዎች ጥራት ያላቸው ግልጽና ለመረዳት ማያስቸግር እንዲሁም ተዓማንነት ያላቸው እንዲሆኑ ለማድረግ በተለየ ትኩረት ሊሰራ የሚገባው ነው፡፡

 

በመጨረሻም የተከፈተው ዌብሳይት ሳቢና ለተመልካች የማይሰለች እንዲሆን መረጃዎችን ወቅታዊ ከማድረግ እንዲሁም በቂ ተከታይ እንዲኖረው በማስተዋወቅ ሁሉም የሚጠብቅበት እንዲወጣ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ፡፡