የኤጀንሲው ስልጣንና ተግባር
ኤጀንሲው እንደ የአከባቢው ነባራዊ ሁኔታ በክልሉ ውስጥ የአማራጭ ኢነርጂ ዓይነቶችን በማጥናት ያለማል፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ የግል ድርጅቶችን በልማቱ የሚሳተፉበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣ያስተዋውቃል፡፡
ለህብረተሰቡ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎችና ለተቋማት ኢነርጂን በቁጠባ የመጠቀም ብቃት ከፍ ለማድረግ የሚረዱ ስልጠናዎችንና የቴክኒክ ደጋፍ ይሰጣል፣ተግባራዊነቱንም ይከታታላል፡፡
አማራጭ ኢነርጂና የኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን በምርምር ያሻሽላል፣ያላምዳል፣ እንዲሁም በክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ መሰረት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እንዲፈልቁ ሃሳብ ያቀርባል፣ ያስተዋውቃል፣ እንዲሰራጩም ያደርጋል፡፡
ለማዕድን ልማት አስተዳደር የአጠቃቀም መመሪያና የሥልጠና ማኑዋል ያዘጋጃል፤ የምርምር ግኝት ለሆኑት የኢነርጂና የኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን ስታንዳርድ ያወጣል፤ ጥናትና ቁጥጥር ያደረጋል፤ ስታንዳርዱም እንዲጠበቅ ይከታተላል፡፡
በክልሉ አግባብነት ያላቸውን ጂኦሎጂያዊ ጥናቶችና ምርመራዎችን እንዲሁም የማዕድናት ፍለጋ ጥናት ያካሂዳል፤ እንዲጠና ያደርጋል፤ የጥናት ውጤቶችንና ግኝቶችን ያሰራጫል፤ሀብትንም ያስተዳድራል፡፡
የማዕድን ልማቶችን የአከባቢን እና የህብረተስብ ደህንነት በጠበቀና ተጠቃሚነቱን በሚያረጋግጥ መልኩ መፈጸሙን ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ያረጋግጣል፣ ይከታተላል፡፡
በሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ለሚካሄዱ የማዕድናት ፍለጋ፣ ምርምራና የማምረት ሥራ እና የከበሩ ማዕድናት አዘዋዋሪነት ፍቃድ ይሰጣል፤ ያስተዳደራል፤ ይቆጣጠራል፤ የሮያሊቲ ክፍያዎችን ይወስናል፤ይሰበስባል፡፡
ህገወጥ የማዕድን ምርትና ዝውውርን ይቆጣጠራል፤ በህገወጥ መንገድ ተይዘው የተገኙ ማዕድናትን በአግባቡ ተጠብቀው ህጋዊ ውሳኔ እንዲያገኙ ያደርጋል፤
የተፈጥሮና የስራ አከባቢ ደህነንትንና የአመራረት ስርዓትን በአዋጅ እና ደንቦች መሰረት መከናውናቸውን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ ስራዎቹም ከአከባቢ ደህነንትና ከሰው ልጅ ጤንነት ጋር በተጣጣመ መልኩ ቀጣይነት እና ዘላቂነተ ባለው ሁኔታ መተግባራቸውን ይከታተላል ይቆጣጠራል፡፡
ለማዕድንና ኢነርጂ ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ይሰጣል፡፡
እንደ የአከባቢው ነባራዊ ሁኔታ በክልሉ ውስጥ የአማራጭ ኢነርጂ ዓይነቶችን በማጥናት ያለማል፣
መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ የግል ድርጅቶችን በልማቱ የሚሳተፉበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣ያስተዋውቃል፡፡
ለፒኮና ማይክሮ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ የሚውሉ ወንዞችንና አማራጭ የሃይል ማመንጫዎችን ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣የኢነርጂ አምራቾችን፣አልሚዎችንና ቴክኒሽያኖችን ያሰለጥናል፣ያበቃል፣የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፡፡
በክልሉ ለሚካሄዱ የአማራጭ ኢነርጂ ግንባታ፣ ተከላና ስርጭት ስራዎች በስታንዳርዱ መሠረት መሆኑን ይከታተላል፤ይቆጣጠራል፡፡
በሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ለሚካሄዱ የማዕድናት ፍለጋ፣ ምርምራና የማምረት ሥራ እና የከበሩ ማዕድናት አዘዋዋሪነት ፍቃድ ይሰጣል፤ያስተዳደራል፤ ይቆጣጠራል፤ የሮያሊቲ ክፍያዎችን ይወስናል፤ይሰበስባል፡፡
ኤጀንሲው አላማውን ለማስፈጸም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 