በሀድያ ዞን ጎምቦራ ወረዳ ከ10.8 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደረገ ።
cerwater
Mon, 05/25/2026 - 09:03
ግንቦት 14/2018 (ወልቂጤ)
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀድያ ዞን ጎምቦራ ወረዳ ከ10 ሚሊዮን 800 ሺህ ብር በላይ ወጪ የተገነባው የ“ኦለዊቾ ለምቡዳ” ንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል ።
ፕሮጀክቱን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) በክብር እንግድነት መርቀውታል ።
ፕሮጀክቱ ከ13 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል ።
የኦላዊቾ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በክልሉ ዋን ዋሽ ፕሮግራም የተገነባ ነው ።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ፣ የክልል ተወካይ ወ/ሮ ታደለች አማኑኤል እና የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ እቴነሽ ሙሉጌታን ጨምሮ ፣ የክልል፣ የዞን፣ የሀብቾ ከተማ እና የጎምቦራ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
See less
Image
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 