ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር እየተሰራ ያለው ስራ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው:- መሀመድ ኑሪዬ (ዶ/ር)
(ሆሳዕና፣ግንቦት 14/2018 ዓ/ም) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድንና ልማት ቢሮ በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ የአንደኛ ጤፎ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አስመርቋል።
በምርቃት መርሃ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሀላፊ መሀመድ ኑሪዬ(ዶ/ር) አካባቢው ከፍተኛ የውሃ ችግ ያለበት በመሆኑ ለማህበረሰቡ ትልቅ እፎይታ በመስጠት የህዝብ መልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ የሰጠ መሆኑንም ተናግረዋል።
በሀገራችን ብልፅግና ተረጋግጦ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር እየተሰራ ያለው ስራ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው ብለዋል።
የለውጡ መንግስት የሰው ተኮር ነው ያሉት ዶክተር መሀመድ ዛሬ የተመረቁት ሁለቱም ፕሮጀክቶች የዚሁ ማሳያ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ውሃ ህይወት ነው ያሉት ዶክተር መሀመድ የውሃ ፕሮጀክት ከፍተኛ ሀብት የሚጠይቅ በመሆኑም ከመነሻው ጀምሮ የአካባቢ ጥበቃ ስራ በተገቢው በመስራት የገፀምድርና የከርሰምድር የውሃ ሀብት በዘላቂነት መንከባከብ ይገባል ብለዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ እንደተናገሩት ጥራት ያላቸው የመጠጥ ውሃ ተቋማትን በመገንባት የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግርን ለማቃለል በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።
የውሃን ችግር መቅረፍ የጤናን፣ የትምህርትን የግብርናንና ሌሎችንም ልማቶች ማስቀጠል በመሆኑ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።
የአንደኛ ጤፎ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ከ126 ሚሊዩን ብር በላይ ወጪ የተገነባ መሆኑን የተናገሩት ሀላፊው 9 ኪ.ሜ የሚሸፍን ዝርጋታ የተደረገለት 9 የውሃ ቦኖዎች እና 7 የእንስሳት ማጠጫ ገንዳዎች ያሉት ከ10 ሺ በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት የሚሰጥ ነው ብለዋል።
በኢፌድሪ የውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር የመጠጥ ውሃና ሳንቴሽን መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ታምሩ ገደፉ እንደተናገሩት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሀገሪቱ የውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች በመቅረፅ የዜጎችን የውሃ ችግር ለመቅረፍ እየሰራ ነው ብለዋል።
በሀገራችን በድርቅ በሚጠቁና በበረሃማ አካባቢዎች በአለም ባንክ ድጋፍ የሚተገበር ፕሮጀክት እንደሀገር በ55 ወረዳዎች እየተተገበረ መሆኑን በዚህ ክልልም በሦስት ወረዳዎች እየተተገበረ መሆኑን አመልክተዋል።
ፕሮጀክቱ የፍሎራይድ ማጣራት የተገጠመለት በመሆኑ ከዚህ ቀደም በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ የሚያስትለውን ጉዳት የሚያስቀር መሆኑንም ተናግረዋል።
የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን ሁሴን በበኩላቸው እንደተናገሩት በዞኑ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በርካታ የመጠጥ ውሃና ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ውሃ በሌለበት ልማት አይታሰብም ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ይህን ውድ ሀብት በተገቢው ማስተዳደርና መጠበቅ ከሁሉም ይጠበቃል ብለዋል።
የለውጡ መንግስት ፍሬ የሆኑት በዛሬው እለት የተመረቁት የበሸኖ የሶላር ፕሮጀክት እና የአንደኛ ጤፎ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በአጠቃላይ ከ167 ሚሊዮን በላይ ወጪ የተደረገበት መሆኑ ተገልጿል።
የክልሉ መንግስት ኮምኒኬሽን
See less
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 