በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በ1ኛ ጤፎ ቀበሌ ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባ የውሃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት እየተመረቀ ይገኛል።
ግንቦት 14/2018 (ወልቂጤ)
በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በ1ኛ ጤፎ ቀበሌ ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ የተገነባ የውሃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መሀመድ ኑሪዬ ፣ የክልሉ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት እየተመረቀ ይገኛል።
በሆርን ኦፍ አፍሪካ ፕሮግራም የገንዘብ ድጋፍ በወረዳው የተገነባው የውሃ ማስፋፊያ ግንባታ ፍሎራይድ ትሪትመንትና ኤሌክትሮሜካኒካል ዝርጋታን ያጠቃለለ እንደሆነ ተገልጿል።
ከአስር ሺ በላይ የአንደኛ ጤፎ እና አጎራባች ህዝቦችን ተጠቃሚ እንደሚያደሮግ የተገለፀው የውሀ ማስፋፊያው 9 የመጠጥ ውሀ ቦኖ፣ 7 የከብቶች ውሀ ማጠጫ ገንዳ፣ ለጤና ጣቢያና ሀይስኩል ወተር ታፕስ ሁለት ቧንቧ፣ ባለ 100 ሜ ኪ ኮንክሪት ሪዘርቫየር አንድ፣ 2 ባለ 50 KVA ትራንስፎርመር እና 2 ኪሎሜትር መስመር ዝርጋታ፣ ዘመናዊ የውሃ ማጣርያ(ፍሎራይድ ትሪትመንት) 3 ሲሊንደር ያለው፣ የተለያዩ አገልግሎት የሚሠጡ 3 ክፍሎች ያሉት እንደሆነ ተገልጿል።
በምረቃ መርሀ - ግብሩ ላይ በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተደድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መሐመድ ኑርዬ፣ የክልሉ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሀ ሰንቴሽን መሪ ስራ አስፈፃሚ ታምሩ ገደፋ፣ የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባዔ ክብርት መነቴ ሙንድኖ፣ የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን ሁሴን ፣ የሆርን ኦፊ አፍርካ ፕሮጀክት አስተባባሪዎች እና ሌሎች የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች በመሳተፍ ላይ ሲገኙ ምረቃውን አስመልክቶ የተለያዩ መልዕክቶች በመተላለፍ ላይ ይገኛል ።
See less
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 