Skip to main content

በዩኒሴፍ በጀት ድጋፍ ከ40 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የበሸኖ ስንቢጣ ሶላር ፕሮጀክት ተመረቀ

ግንቦት 14/2018 ዓ/ም)

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ በሀላባ ዞን በዌራ ጂጆ ወረዳ ለንጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት እንዲውል ያስገነባውን በሸኖ ስንቢጣ ሶላር ፕሮጀክት አስመረቀ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ ባስተላለፉት መልዕክት የክልሉን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግርን በመፍታት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።

የንፁሁ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ወደ ሶላር ኢነርጂ መቀየሩ በዘላቂ ታዳሽ ሀይል አማራጭ የማህበረሰቡ የነዳጅ ወጪ በማስቀረት አስተማማኝ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን አቶ ዳዊት ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ አሁን ያለውን የኢነርጂ ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ ዘላቂ መፍትሄ መሆኑንም ሀላፊው አብራርተዋል።

በዩኒሴፍ በጀት ድጋፍ ከ40 ሚሊዩን ብር በላይ ወጪ የተገነባውና 360 የሶላር ፓኔሎች የተተከለበት 211 ኪሎ ዋት ሀይል የሚያመነጭ መሆኑን ጠቁመዋል።

በወረዳው የሚገኙ ሰባት ቀበሌያት ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑ በቀጣይ አራት ቀበሌያትም የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሚሆኑ መሆኑን ተናግረው በዚህም ከ40ሺ በላይ የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።

ፕሮጀክቱ የክልሉ ውሃ፣ መስኖ ማዕድን ልማት ቢሮ ከከፌዴራል ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና ከዩኒሴፍ ጋር በመተባበር ያስገነባው መሆኑ ተገልጿል።

በመርሃ ግብሩ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሀላፊ መሀመድ ኑሪዬ(ዶ/ር) ጨምሮ የክልል የፌዴራል እና የሀላባ ዞን ከፍተኛ አመራሮችና የአካባቢው ማህበረሰብ ተገኝተዋል።

የክ/መ/ኮ

See less

Image