Skip to main content

ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ የሳንኩራ ባለብዙ መንደር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ምርቃት ላይ ያስተላለፉት መልዕክት ።

ግንቦት 13/2018 ዓ.ም (ወልቂጤ)

የክልሉ መንግስት የሕዝቡን ኑሮ ለማመጣጠን ሰፊ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ይህንን ለማጠናከር የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሚጠበቅበትን ይወጣል ።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለዜጎች ንፁህ የመጠጥ ውሃና የሳኒቴሽን አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የሰራው ፕሮጀክት የውሃ ሀብታችን ለብልፅግናች የሚለውን መርህ የሚያረጋግጥ ነው ።

የውሃ ሀብትን በተገቢው መንገድ ማስተዳደርና ለዘላቂ ልማት ለማዋልና ከሚሰሩ በርካታ ስራዎች መካከልም ለሳኒቴሽን ዘርፉም ልዩ ትኩረት ስለሚያስፈልግ ፕሮጀክቱን አጠናቀን ለህብረተሰቡ ስናስረክብ፤ መንከባከብ ብቻ ሳይሆን ብክነትንና ብክለት በመቀነስ፣ ውሃውን በቁጠባ መጠቀምና የውሃ አገልግሎት ተቋም በሚዘረጋው የክፍያ ስርዓት ክፍያቸውን በወቅቱ እንዲከፍሉም ሊሰራ ይገባል ።

ንፁህ የመጠጥ ውሃ ህይወትን ለማስቀጠል አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች ውስጥ ተጠቃሽ በመሆኑ ውሃ ባለበት ቦታ ሁሉ ህይወት እንዲቀጥል ምክንያት ስለሆነም፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የውሃ ሀብትን ማስተዳደር የሚያስችል የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት እየሰራ ይገኛል።

ለፕሮጀክቱ ስኬት ከፍተኛ በጀት የተመደበ ሲሆን ለህብረተሰቡ ጤና፣ ለሴቶችና ለህፃናት፣ ለትምህርት ብሎም ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናን ለማቅለል የላቀ ሚና አለው ።

ፕሮጀክቱ የሚገኝባቸው አካባቢ ስነ ምህዳር በተገቢው መንገድ መጠበቅ ይገባል ።

ፕሮጀክቱ ዘለቄታዊ አገልግሎት እየሰጠ እንዲቀጥል የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ቴክኒካዊ ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።

ፕሮጀክቱ የሕዝብ ስለሆነ ውሀውን ለማስተዳደር የተመደቡ አካላትን በተገቢው መደገፍ ይገባል ።

See less

Image