በክልሉ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች ውጤታማ ናቸው:-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
(ሆሳዕና፣ግንቦት 18/2018) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሀዲያ ዞን በሾኔ ከተማ አስተዳደር የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ስራ አስጀመሩ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በፕሮጀክቶች ምረቃ ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት በክልሉ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች ውጤታማ ናቸው ብለዋል።
በከተማ አስተዳደሩ ከተመረቁት ፕሮጀክቶች ውስጥ የሾኔ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ከ88 ሺ በላይ ህዝብ ተጠቃሚ ማድረጉን ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።
በዛሬው እለት የተመረቁት የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት ያለ ምንም እንከን አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ህብረተሰቡ ልዩ ጥበቃና እንክብካቤ እንዲያደርግ ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።
ውሃ ለሰው ልጆች ህይወት እና ለኑሮ መሰረት ወሳኝ ነው ያሉት
ርዕሰ መስተዳድሩ ብልጽግና ፓርቲ በሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶቹ የጀመራቸውን ስራዎች ይበልጥ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በዛሬው እለት የተመረቀው የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽ/ቤት ወንጀልን አስቀድሞ በመከላከል ረገድ የሚኖረው አበርክቶ ከፍተኛ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል።
የልማት ፕሮጀክቶቹ ተጠናቀው ለውጤት እንዲበቁ ላደረጉ ከፌደራል እስከ ክልል፣ወረዳና ከተማ አስተዳደር ስራውን ለመሩ እና ላስተባበሩ አካላት ርዕሰ መስተዳድሩ ምስጋና አቅርበዋል።
ብልጽግና የሚመራው መንግስት በ2023 እና በ2040 በአፍሪካ እና በአለም አቀፍ ደረጃ አብነት ለመሆን እየተጋ ያለ ፓርቲ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል።
ይህን የፓርቲውን አላማና ግብ በመገንዘብ ህዝቡ ላሳየው ጥልቅ ፍቅር እና ድጋፍ ርዕሰ መስተዳድሩ በራሳቸው እና በክልሉ መንግስት ስም ምስጋና አቅርበዋል።
የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቲዮስ አኒዮ እንደገለጹት የሾኔ ከተማ አስተዳደር ህብረተሰብን በማሳተፍ ውጤታማ የልማት ስራ ማከናወን መቻሉን በአብነት ጠቅሰዋል።
አካባቢውን የሰላም እና የለውጥ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የክልሉ መንግስት የልማትፕሮጀክቶች ስኬታማ እንዲሆን የላቀ ድጋፍ ማድረጉን አብራርተዋል።
የሾኔ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አበራ በዶሬ በበኩላቸው የለውጡ መንግስት ሀገሪቱን ተረክቦ ወደ ስራ ከገባበት ማግስት ጀምሮ ከተማዋ በፈጣን እድገት ላይ ትገኛለች ብለዋል።
በ350 ሚሊየን ብር የተገነባው የሾኔ ከተማ አስተዳደር የውሃ ፕሮጀክት የህብረተሰቡን መሰረታዊ የውሃ ፍላጎት እውን የሚያደርግ መሆኑን ከንቲባው አስረድተዋል።
በላሎ ገርቤ ቀበሌ በዠየታዳሽ ሀይል ውሃ ፕሮጀክት ደግሞ ሌላኛው የልማት ስራችን ስኬታማነት ማሳያ ነው ሲሉም አቶ አበራ ጠቁመዋል።
በህብረተሰብ ተሳትፎ ተገንብቶ ለምረቃ የበቃውና የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት አካል የሆነው የፖሊስ ጽ/ቤት የከተማ አስተዳደሩን የልማት ስራ ስኬታማ ያደርገዋል ብለዋል።
በከተማው የተመረቁት የውሃ ተቋማት 800ሺ ሊትር የሚይዙ የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች፣5 ቦኖዎች፣ 42 ኪ/ሜትር የሚሸፍኑ የውሃ መስመሮች፣እንዲሁም 16 ኪ/ሜ መሸፈን የሚችል ዋና መስመር ያካተተ መሆኑን ከንቲባው ተናግረዋል።
በምረቃ መርሐ ግብሩ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር ) በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኢንዱስትሪ ክላስተር አስተባባሪና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤል፣በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ መሐመድ ኑሪዬ (ዶ/ር )የክልል እና የሀዲያ ዞን የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የክልሉ መንግስት ኮምኒኬሽን
See less
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 