Skip to main content

ስምንት የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ግንባታ ስራ ለማከናወን ከአሸናፊ ተቋራጮች ጋር የቦታ/ሳይት ርክክብ ማድረጉን የክልሉ ውሀ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ አስታወቀ ።

ግንቦት 27/2018 (ወልቂጤ)

በክልሉ ስድስት አዲስና በተለያዩ ምክንያቶች ግንባታቸው የዘገዩ ሁለት ነባር ፕሮጀክቶች ቤት/ሳይት በማስረከብ ወደ ስራ በማስገባት የህብረተሰቡን የንፁህ መጠጥ ዉሃ ፍላጎት ለማሟላት እየተሠራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ አስታወቀ ።

‎የክልሉ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ የመጠጥ ውኃ ግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገረሙ አቡና በርክክቡ ወቅት እንደገለፁት ቢሮዉ በተለያዩ ምክንያቶች የተጓተቱ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማሟላትና ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል ፡፡

‎በኤስዲጂ ፕሮግራም በጀት የሚሰሩ 7 ፕሮጀክቶች በካፒታል በጀት የሚከናወን እንድ ፕሮጀክት ጨረታ በማውጣትና አሸናፊ ከሆኑ ተቋራጮች ጋር ቀደም ሲል የክልሉ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ውል መፈራረሙን ያስታወቁት አቶ ገረመው ግንባታ ለማስጀመር ከተቋራጮቹ ጋር የሳይት ርክክብ መደረጉን ገልፀዋል።

‎ቢሮው ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው ጊዜና ጥራት ተጠናቀው ለህብረተሠቡ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በትኩረት ይሰራል ያሉት አቶ ገረመው ግንባታው በሚከናወንባቸው አካባቢዎች የሚያጋጥሙ ችግሮችን ከመንግስትና ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጅት እንዲፈታ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

‎የሳይት ርክክብ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች ገረምቦ፣ አለላ፣ ፣ጊምቢቾ ፣ ማሬ ፣ሀንሻ ቁ.2 ፣ኤሎስ ፣ወዶ ውሪብ እና የጉንቹሬ ፕሮጀክቶች መሆናቸውን ያብራሩት ዳይሬክተሩ እነዚህም በክልሉ በጉራጌ ፣በሀዲያ ፣በሀላባ ፣በከምባታና በስልጤ ዞኖች የሚገኙ መሆናቸውን ተናግረዋል ፡፡

‎ከፕሮጀክቶቹ መካከል ጊምቢቹና ማሬ ውጪ ሌሎቹ አዳዲስ ፕሮጀክቶች መሆናቸውንም አመላክተዋል።

‎በሳይት ርክክቡ ላይ አግኝተን ያነጋገርናቸው የተቋራጭ ድርጅት ስራ-አስኪያጆች በሰጡት አሰተያየት ግንባታውን ውል በገቡት ጊዜና ጥራት ጨርስው ለማስረከብ በሙሉ አቅማቸው እንደሚሠሩ ገልጸው ለዚህም ውጤታማነት በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት ፣ ባለድርሻ አካላትና የአካባቢው ማህበረሰብ ከጎናቸው እንዲቆም አስታውቀዋል ፨

‎ያነጋገርናቸው አንዳንድ የአከባቢው ነዋሪዎችም በሰጡት አስተያየት ከፍተኛ የሆነ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት መኖሩን ገልፀው ለተሰጣቸው እድል ምስጋናቸው አቅርበዋል ፡፡

‎በግንባታው ሂደት የሚያገጥሙ ችግሮችን በመቅረፍ የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውንም ገልፀዋል ፡፡

‎በሳይት ርክክብ መረሃ ግብሩ ላይ የየዞኑ ውሃና ኢነርጂ መመሪያ ኃላፊዎች፣ የወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎች፣የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች ፣አሸናፊ ተቋራጮች ፣የዉሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ከፍተኛ ባለሞያዎች እንዲሁም የየአካባቢው ማህበረሰብና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

See less

Image