በሀላበ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ በጢጣሊ-ብጦራ እና በንሸኮራ ቦጢ ቀበሌ በ Give Water ፕሮግራም የተገነባው የንጽሁ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ።
cerwater
Fri, 07/03/2026 - 10:20
ሰኔ 23/2018 (ወልቂጤ)
በዌራ ዲጆ ወረዳ ውሃ ማዕድን ኢነርጂ ጽ/ቤት አማካኝነት በጢጣሊ-ብጦራ እና በሀንሸኮራ ቦጢ ቀበሌ በ Give Water ፕሮግራም የተገነባው የንጽሁ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል።
የንጽሁ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ 14 ሚሊዮን ብር የፈጀ መሆኑን ከወረዳው ውሃ ማዕድን ኢነርጂ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በምረቃው ፕሮግራም የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን ሁሴን፣ የሀላባ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ መሐመድ አሚን ሀጂ ማህዲ ፣የሀላባ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መሐመድ ከማል ኑሪዬ፣የዌራ ዲጆ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዲ አደምን ጨምሮ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮችና የ Water TURKIYE DIYANE VAKFI ፕሮግራም አስተባባሪ አካላት የቀበሌ ህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮምኒኬሽን ዘግቧል ።
See less
Image
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 