በHuman capital operation ፕሮግራም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ አስታወቀ ።
ሰኔ 22/2018 (ወልቂጤ)
በክልሉ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የHuman capital operation ፕሮግራም ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 ዕቅድ ማስተዋወቂያ መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሄዷል ።
በመድረኩ የተገኙት በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የክልሉ ውሀ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ምክትልና የዉሀ ሀብት ጥናት አሰተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አለይካ ሽኩር እንደገለፁት በHuman capital operation ፕሮግራም ባለፉት ጊዜያት በትምህርት ውጤት ማሻሻል ፣ በህፃናት አይምሮ መቀንጨር መከላከልና በመንግሥት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል ላይ በሀላባ ዞን በዌራ ወረዳ እና አቶቴ ኢሉ ወረዳ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች መከናወኑን ገልፀዋል ።
በፕሮግራሙ የተቀመጡ ግቦችን 100% በማሳካት ተጨማሪ እድሎች ለማግኘት ተግባራት በተቀመጠላቸው ጊዜ መፈፀምና ወቅቱን የጠበቀ ሪፖርት በማዘጋጀት በተጠያቂነት ለሚመለከታቸው ተደራሽ እንዲሆን መስራት እንደሚገባ ወ/ሮ አለይካ አመላክተዋል ።
የቢሮው ምክትል ኃላፊና የመጠጥ የውሃ ሀብት፣ ጥናትና ዲዛይን አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ አየለ ኬርጋ (ኢ/ር) የወረደውን ፕሮግራም በአግባቡ ለመተግበር በአመራር ደረጃ መገምገምና በፕሮግራሙ ተጠቃሚ ከሆኑ አቻ ሴክተሮች ጋር በማቀናጀት ረገድ በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል ።
እንደ ክልል ፕሮጀክቶችን ጀምሮ በመጨረስ እየተመዘገበ ያለውን ውጤታማነት በHCO ፕሮግራም ለመድገም በቀሪ ጊዜያት መረባረብ እንደሚገባ ኢ/ር አየለ አያይዘው ገልፀዋል ።
በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ የውሃ ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድሻፊ አሰሞ በሰጡት አስተያየት የHCO ፕሮግራም የንፁህ መጠጥ ውሃ በትምህርት ፣በጤና ተቋማትና በማህበረሰብ ተደራሽ በማድረግ የወረዳው የውሃ ሽፋን ከፍ ለማድረግ በርካታ ተግባራት መከናወናኑን ተናግረዋል ።
በበጀት ዓመቱ በወረዳው በተለያዩ ቀበሌያት በመጠጥ ውሃ ፣በትምህርት ፣በጤናው ዘርፍ እስከ 8ሺ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል ።
በተመሳሳይ የአቶቴ ኢሉ ወረዳ የHCO ተወካይ አቶ አብዲ ሎላሶ በበኩሉ ፕሮግራሙ በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች በንፁህ መጠጥ ውሃ ማስፋፊያ በጤና በትምህርትና በሌሎች ዘርፎች 7ሺ የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራት መከናወን መቻሉን ተናግረዋል ።
የተጀመሩ ሥራዎች እንዳይጋተቱ የግዢ አፈፃፀምን ጨምሮ ሌሎች ማነቆዎችን በወቅቱ መፍታት እንደሚገባ የመድረኩ ተሳታፊዎች ገልፀዋል ።
ለመድረኩ የተዘጋጀ የ2018 በጀት ዓመት HUMAN CAPITAL OPERATION ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2019 ዕቅድ በቢሮው የበጀት፣ ዕቅድ ፣ ዝግጅት ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ስዩም ቀድሩ እና በሁለቱ ወረዳ አካላት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ።
በመድረኩ የክልሉ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ አማካሪ አቶ ሀይሌ ደዊ ጨምሮ ከቢሮው፣ ከሀላባ ዞን ውሀ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ እንዲሁም ከሁለቱ ወረዳዎች የሚመለከታቸው ተገኝተዋል ።
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 