በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በቢሮውና ተጠሪ ተቋማት ከተመዘገቡ ስኬቶች መነሻ በ2019 የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንደሚሰራ የክልሉ ውሀ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ አስታወቀ ።
ሰኔ 10/2018 ዓ.ም (ወልቂጤ)
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ከተጠሪ ተቋማት ጋር ግምገማ ነክ ውይይት በወልቂጤ ከተማ አካሄዷል ።
የክልሉ የውሃ ፣መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ እንደተናገሩት በ2018 በጀት ዓመት በክልሉ በመጠጥ ውሃ፣ በመስኖና በማዕድን ኢነርጂ የተመዘገቡ ስኬቶችን መነሻ በማድረግ በተያዘው በጀት ዓመት ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚሰራ ገልፀዋል ።
በተጠናቀቀው በጀት በክልሉ መንግስት ቁርጠኛ አመራር ሰጪነት በተወሰደው ርምጃ ለበርካታ አመታት የመልካም አስተዳደር ችግር ሁነው የሰነበቱ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን መልሶ ወደ ግንባታ ስራ በማስገባትና በማጠናቀቅ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻሉን አመላክተዋል ።
ባለፉት ጊዜያት በክልሉ የተካሃዱ የውሃ ተቋማት ቆጠራና የውሃ ሽፋን ውጤት ከክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር መድረኮችን በመፍጠርና በማረጋገጥ የክልሉ የገጠርና የከተማ መጠጥ ውሃ ሽፋን ሰነድ የማፅደቅ ስራ ተከናውኗል።
በተያያዘ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተቋማት ዘላቂ አገልግሎት እንዲሰጡ በዋን-ዋሽ ፕሮግራም ድጋፍ ከስልሳ ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ በመፈፀም ከጀነሬተር ወደ ትራንስፎርመር የመቀየር ትግበራ በመገባት ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
በዉሀ ሀብት ጥናት አስተዳደር፣ በጥናትና ዲዛይን ፣ በውሀ ተቋማት አደረጃጀት እና በሌሎች ዘርፎች በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አበረታች ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል ።
እንደ ሀገር በልዩ ሁነታ የተጀመረውን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በመሸጋገር የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት በክልሉ በመስኖ ዘርፍ የተሠሩ ተግባራት ትልቅ ሚና አላቸው ብለዋል።
በ2018 በጀት ዓመት በክልሉ ተመርቀው ወደ ስራ የገቡ በርካታ የመስኖ ተቋማትን ምርታማነት በመጨመር የኑሮ ውድነት እንዲቀነስ ዘርፉ ትልቅ አሰሰተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል።
በኮንስትራክሽንና፣ በኢንዱስትሪና በማዕድን በተጠናቁቀው በጀት ዓመት ከእቅድ በላይ መፈፀሙን የገለፁት አቶ ዳዊት በ2019 በርካታ የክልሉን የማዕድን ሀብቶች አግባባዊ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ ለማዋል የክልሉ መንግስት ልዩ ትኩረት በመስጠቱ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል ።
በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ይደርስ የነበረውን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል ከፌደራል ውሃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በተሠራው ሰራ ይደርሱ የነበሩ አደጋዎች በከፍተቸኛ ደረጃ መከላከል ተችሏል ብለዋል።
አቶ ዳዊት አክለውም ከጊዜ ወደጊዜ እየተሻሻለ የመጣው የቢሮው የመፈፀም አቅም በመጠቀም አሁን ካለው የህዝባችን ፍላጎት መሠረት ያደረገ የተሻለ ስራ ለመስራት የድጋፋዋ ክትትል ስራና የአቅም ግንባታ ስራዎች እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል ።
የክልሉ የመስኖ ተቋማት ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ ካሳዬ ተክሌ (ኢ/ር) እንደተናገሪት በ2018 በጀት አመቱ 610 ሄ/ር የሚያለሙና 2300 አባዎራና እማዎራ ተጠቃሚ የሚያደርጉ አምስት የመስኖ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ መቻሉን ገልፀው በአዲሱ በጀት ዓመት በተለያዩ ምክንያቶች ያላለቁ እና አዳዲስ የመስኖ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል ።
የክልሉ ማዕድን ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን መኔዶ በበኩላቸው በክልሉ በማዕድን ዘርፍ ያለውን እምቅ አቅም ለመጠቀምና የኢነርጂ ውጤቶችን ተደራሽ በማድረግ ተሞክሮዎችን ወደ ሁሉም መዋቅሮች በማስፋት በ2019 በሰፊው ታቅዶ እንደሚሰራ ገልፀዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የቢሮውና የተጠሪ ተቋማቱ የስራ ሃላፊዎች እና ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት የአመቱን አፈፃፀምና ቀጣይ እቅድ በተደራጀና በተጠናከረ መንገድ መገመገም መቻሉ ተግባርን በሀላፊነትና በተጠያቂነት ለመወጣት እንደሚያዘጋጃቸው ገልፀዋል ።
በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት የተግባርና የመልካም አስተዳደር እቅድ በቢሮውና ተጠሪ ተቋማት የእቅድ በጀት ዝግጅትና ክትትል ግብረ መልስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች በኩል ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ።
በመድረኩ የቢሮውና የተጠሪ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች እና የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል ።
See less
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 