Skip to main content

የማህበረሰቡን የመጠጥ ውሃ እጥረት ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ እንደሚገኝ የማረቆ ልዩ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት አስታወቀ ።

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረቆ ልዩ ወረዳ የማህበረሰቡን የንጹህ መጠጥ ውሃ እጥረትን ለማቃለል በግራር ቤት ተሀዲሶ ማህበር አማካኝነት 8 መለስተኛ ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገልፆአል።

በልዩ ወረዳው ዲዳ ሀሊቦ፣ በኩኖ ቀርጠፋ፣ በኩኖ አሌመናና በሆቤ ጀሬ ደምበቃ ቀበሌዎች የተጀመረው የ8 መለስተኛ ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል ተብሏል።

የማረቆ ልዩ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ ዘካርያስ ባንደ ንጹህ መጠጥ ውሃ የማህበረሰቡ መሠረታዊ ጥያቄ መሆኑን በማንሳት ተቋሙ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አከላት ጋር ዘርፋ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ተነግረዋል።

በልዩ ወረዳው በግራር ቤት ተሃድሶ ማህበር አመካኝነት የተጀመረው የ8 መለስተኛ ጉድጓዶች ቁፋሮ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ከ5250 በላይ የአከባቢ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል ።

በተመሳሳይ የልዩ ወረዳ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ከድር ኬናሞ በበኩላቸው ከዚህ ቀደም በብልሽት ምክንያት አገልግሎት ያቋረጡ ተቋማትን ከመጠገን ባለፈ፣ አዳዲስ የሚገነቡት መለስተኛ ጥልቅ ጉድጓዶች ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲጠናቀቁ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ በማንሳት የውሃ ተቋማቱ ተገንብተው ለአገልግሎት በሚበቁበት ወቅት ማህበረሰቡ ተቋማቶቹን የመጠበቅና የመንከባከብ ኃላፊነት እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ሲል ከልዩ ወረዳው ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

See less

Image