በዋን ዋሽ ሴክተሮች የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች አፈፃፀምን በጥብቅ ዲስፕሊን መምራት እንደሚገባ ተገለፀ ።
ሃምሌ 14/2018 (ወልቂጤ)
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የዋሽ ሴክተሮች የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምና የ2019 እቅድ መገምገሚያ መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሄዷል ።
በዋን ዋሽ ፕሮግራም የቻናል አንድ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ታረቀኝ ኑራሞ እንደተናገሩት በ2018 በጀት ዓመት በዋን ዋሽ ሴክተሮች እቅድ አፈጻጸም ላይ የታዩ ጥንካሬዎችን ለ2019 በጀት እቅድ እንደግብአት በመጠቀም መዋቅሮች በማቺንግ ፈንድ የሚጠበቅባቸውን ገንዘብ ባጠረ ጊዜ ውስጥ በማስገባት ከወዲሁ ወደ ስራ መግባት እንደሚጠበቅባቸው እና የፕሮጀክቶቹን አፈፃፀም በጥብቅ ዲስፕሊን መምራት እንደሚገባ ተናግረዋል ።
በተወሰኑ አካባቢዎች በተገነቡ ፕሮጀክቶች የፋይናንሻል እና ፊዝካል አፈፃፀም ላይ የታዩ ልዩነቶችን በማጣጣም የቀጣይ ፕሮግራሞችን በጠንካራ ድጋፋዊ ክትትል መምራት እንደሚገባም አመላክተዋል።
የክልሉ ዋሽ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መካ ሰልማን በበኩላቸው በዋን ዋሽ ሴክተሮች በክልሉ በመተግበር ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባሻገር በክልሉ ጤናማና ተወዳዳሪ ትውልድ በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል።
ለፕሮጀክቶቹ ማስፈፀሚያ በሚል በተወሰኑ ሴክተሮች ለታችኛው አደረጃጀት የሚወርዱ በጀቶች ከፕሮግራሙ ውጪ እንዳይውል ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ እንደሚጠበቅ ያመላከቱት አቶ መካ የፕሮጀክቶቹን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራርን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚጠበቅ ተናግረዋል ።
በዋን ዋሽ ፌዝ-2 ፕሮግራም በዋሽ ሴክተሮች(በውሃ፣ በጤና፣ በትምህርትና በፋይናንስ) በክልሉ በታቀፉ መዋቅሮች
በመጠጥ ውሀ ዘርፍ በአጠቃላይ ከ244 ሺ በላይ ህብረተሰብን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ፣ በገጠር መጠጥ ውሃ 28 የተለያዩ ፕሮጀክቶች እንዲሁም በከተማ 2 የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ግንባታ ስራ የማሳለጥ ስራዎች በመከናወኑ የገጠር ውሀ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ አፈፃፀም እንዳላቸው ተገልፆ የሁለት ከተሞች ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ተብሏል።
በጤናው ዘርፍ በ82 ጤና ተቋማትን በሳኒቴሽንና በውሃ ፋሲሊቲ በሙሉ ዋሽ ፓኬጅ ማጠናቀቅ የተቻለ ሲሆን፣ እንዲሁም በገጠር ዋሽ፣ 484 ቀበሌያትን ከሜዳ ላይ መፀዳዳት ነፃ በማድረግ እና ከ125 ሺ በላይ የቤተሰብ የተሻሻለ ሳኒቴሽን አግልግሎት ላይ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ።
በትምህርት ዘርፍ በ76 ትምህርት ቤቶች የሙሉ ዋሽ ፓኬጅ ማለትም በእያንዳንዳቸው (መፀዳጃ ቤት ለወንድና ለሴት ተማሪዎች ፣ በውሀ ማስፋፊያ ፣ በሴቶች ንጽህና መጠበቂያ) እንዲሁም በ53 ትምህርት ቤቶች የከፊል ዋሽ ፓኬጅ ፋሲሊቲ በማሟላት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን በሪፖርቱ ተመልክቷል። በተጨማሪም ተማሪዎች: የትምህርት ቤት መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞችና ዋሽ ባሀድርሻ አካላት የግል: የአካባቢና የህብረተሰቡን ንፅህና እንዲጠብቁ በርካታ የውሃ ሳኒቴሽንና የግል ንፅህና አያያዝ: አጠቃቀምና ተያያዥ ስልጠናዎች ተሰጥተዋል።
የፋይናንስ ሴክተርም ከገንዘብ ሚኒስቴር የሚተላለፈውን በጀት በአግባቡ በማስተዳደር ለታለመለት ዓላማ እንዲውል በአግባቡ በማስተዳደር፣ በመቆጣጠርና ድጋፋዊ ክትትል በማድረግ የተሟላ ግብረ መልስ በመስጠት ረገድ የፋይናንስ ዘርፉ ትልቁን ድርሻ መወጣት ላይ እንደሚገኝ ተገልፆአል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የዋን ዋሽ ፕሮጀክት የክልሉ መንግስትን የልማት ክፍተቶችን በማጥበብ ከህብረተሰቡና በመንግስት መካከል ጤናማ የሆነ ግንኙነት እንዲፈጠር ጉልህ ድርሻ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል።
የተሰሩ ፕሮጀክቶች ዘላቂ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በመንግስትና በህብረተሰቡ የተጀመረው ተሳትፎና በማጠናከር ፕሮጀክቶቹን በባለቤትነት የመጠበቅና የመንከባከብ ስራ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
See less
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 