Skip to main content

በግራር ቤት ተሃድሶ ድርጅት አማካይነት ለመጠጥ ውሃ አገልግሎት የሚሆን መለስተኛ ጥልቅ ጉድጓድ የውሃ ችግር ባለባቸው ቀበሌዎች እየተቆፈረ ። ሃምሌ 27/2018 ዓ.ም (ወልቂጤ)

በምስራቅ ጉራጌ ዞን ምስራቅ መስቃን ወረዳ በግራር ቤት ተሃድሶ ድርጅት አማካይነት ለመጠጥ ውሃ አገልግሎት የሚሆን መለስተኛ ጥልቅ ጉድጓድ የውሃ ችግር ባለባቸው በተመረጡ ቀበሌዎች ቁፋሮ መጀመሩን የወረዳው ውሃና ማዕድን ኢነርጂ ጽ/ቤት ገለፀ ።

የማህበረሰቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽ ለማድረግ በግራር ቤት ተሃድሶ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር እየተሰራ መሆኑን የምስራቅ መስቃን ወረዳ ውሃና ማዕድን ኢነርጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ሸመክት ገልፀዋል ሲል የወረዳው መንግስት ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።

See less

Image