የቢሮ ኃላፊ መልዕክት
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ መልዕክት
አቶ ዳዊት ሃይሉ ገሮ
ኢትዮጵያ አገራችን በተለያዩ ወንዞች፣ ጅረቶች፣ ሐይቆች እና የውሀ አካላት የታደለች እና በተፈጥሮ ፀጋ የተቸረች ሀገር ከመሆኗም በላይ በአስራ ሁለት ትላልቅ የውሀ ተፋሰሶች የተከፈለች አገር ናት፡፡ ምንም እንኳን የተለያዩ ወንዞችና ሐይቆች ባለቤት ብንሆንም የውሀ ሀብቶቻችንን እንደ ሀገር ሙሉ በሙሉ በተገቢው መንገድ መጠቀም አለመቻላችን በውስጣችን ቁጭት እንዲፈጠር አድርጓል፡፡ ከዚህ አንፃር የውሀ ሀብቶቻችንን እና የተፈጥሮ ፀጋዎቻችንን በአግባቡ በማልማት፣ በማበልፀግና ለዜጎቻችን ምቹና ተስማሚ በማድረግ ጥቅም ላይ ለማዋል የውሀ ሀብቶቻችንን የማልማት፣ የማስተዳደር፣ የመንከባከብ እና በተገበው መንገድ ለመገልገል በመንግስት ረገድ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሰጥ ከላይ ከተገለጹት እንደ አገር ካሉን አስራ ሁለት ተፋሰሶች መካከል ሁለት ትላልቅ የኦሞ ጊቤ እና የስምጥ ሸለቆ ተፋሰሶች በክልላችን በሚገኙ አካባቢዎች የሚያቋርጡና በርካታ የክልልን ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተፋሰሶች ናቸው፡፡ እነዚህ ተፋሰሶች በርካታ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢከኖሚያዊ ጥቅሞች ለክልሉ ማህበረሰብ የሚሰጡ ናቸው፡፡ እንደሚታወቀው የግልገል ግቢ ሁለት የውሀ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በኦሞ ጊቤ ተፋሰስ ላይ የተመሰረተና በየም ዞን ውስጥ የሚገኝ የተፋሰሱ ትልቁ ቱሩፋትና ልዩ ትኩረት የሚፈልግ አካባቢ ነው ተጨማሪ ያንብቡ
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 
