በሳንኩራ ወረዳ የቆሬ ቀበሌ የንፁህ መጠጥ ውሃ ኣገልግሎት ለማስቀጠል በህብረተሰቡ የ4.5 ሚሊዮን ብር አስተዋፅኦ የማሻሻያ ስራዎች መከናወኑ ተገለፀ።
ሐምሌ 25/2018 ዓ/ም
በስልጤ ዞን ሳንኩራ ወረዳ የቆሬ ገጠር ቀበሌ የንፁህ መጠጥ ውሃ ኣገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ከአካባቢው በህብረተሰብ በተገኘ የ4.5 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ የማሻሻያ ስራዎች መከናወኑ ተገለፀ።
የሳንኩራ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን በማስፋትና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቀበሌው የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር ጨምሮ የ4.5 ሚሊዮን ብር የህብረተሰብ ተሳትፎ ወጪ የቆሬ ቀበሌ የገጠር መጠጥ ዉሃና ሳኒቴሽን ማህበርን ከጄነሬተር ወደ መብራት መቀየር የሚያስችል የትራንስፎርመር ተከላ ፕሮግራም መካሄዱ ተገልፆአል፡፡
ተቋሙ በየደረጃው የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ፡
ይህንን ተከትሎ ተቋሙ የቆሬ የንፁህ መጠጥ ውሃና ሳንቴሽን ማህበር ከጀኔሬተር በተጨማሪ በመብራት አገልግሎት መስጠት እንዲችል ሙሉ በሙሉ በህብረተሰቡ ተሳትፎ በተገኘ በጀት ከ4 ሚሊየን 5 መቶ ሺ ብር በላይ ወጪ የ2 ኪሎ ሜትር መስመር ዝርጋታ ፣ የ50 ፖል ተካለ ፣ የ100 KVA ትራንስፎርመር ግዥ በመፈፀም እና አስፈላጊ የሆኑ ቁሰቁሶች እንዲሟላ በማድረግ የወረዳው አስተባባሪ አመራሮች በተገኙበት የትራንስፎርመር ተከላ/ሰቀላ ተካሂዷል፡፡
የቆሬ ቀበሌ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን በዘላቂነት ለማስፋት የውሃ ማህበሩን ከጄኔሬተር በተጨማሪ በመብራት አገልግሎት መስጠት እንዲችል ከህብረተሰቡ ጋር በተደረገ ውይይት አስፈላጊው የገንዘብ አሰባሰብ በማካሄድ ትራንስፎርመርን ጨምሮ አስፈላጊ ቁሳቁሶች ግዢ በመፈጸም የማብራት ዝርጋታ ስራ በማጠናቀቅ ትራንስፎርመር የመስቀል ስራ ተሰርቷል ሲል ከወረዳው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
See less
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 