የክልሉ ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ በአዳፕቴሽን ፈንድ ፕሮግራም ከ29 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የፕሮጀክት ግንባታ ውል ስምምነት ፈፀመ።
መስከረም 7/2019 (ወልቂጤ)
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ በአዳፕቴሽን ፈንድ ፕሮግራም ከ29 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በየም ዞን ፎፋ ወረዳ ለሚገነባው የመስኖ እና የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ጋር የውል ስምምነት ፈጽሟል።
የውል ስምምነቱን የተፈራረሙት በቢሮ ኅላፊ ማዕረግ የክልሉ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ አለይካ ሽኩር እንደገለፁት ፕሮጀክቱ የአየር ንብረት ለውጥ የማይበግረው የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት በማለም እንደ ሀገር በስድስት ክልሎች እና እንደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በግብርና ቢሮ አስተባባሪነት በየም ዞን ፎፋ ወረዳ ላይ በተለያዩ ዘርፎች የሚንቀሳቀስ ሲሆን በውሃው ዘርፍ በመጠጥ ውሃ፣ በመስኖና ኢነርጂ ላይ አተኩሮ ይሰራል ብለዋል።
በዛሬው ዕለት ውል የተገባባቸው የመስኖ እና የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ግንባታ በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ለሕብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ታሳቢ በማድረግ በውል ስምምነቱ የተቀመጠ መሆኑን የገለፁት ወ/ሮ አለይካ ፕሮጀክቶቹ ተጀምረው እስከሚጠናቀቁ የክልሉ መንግስት ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያርግ አስታውቀዋል ።
የውል ስምምነቱ አነስተኛ የመስኖ እና የመጠጥ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ያካተተ ሲሆን የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ስራው እንደተጠናቀቀ የአካባቢውን ህብረተሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ ወደ ማስፈፊያ ስራ እንደሚገባ ወ/ሮ አለይካ አያይዘው ተናግረዋል ።
የውል ተቀባይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ምክትል ስራ አስኪያጅና የምህንድስና ኮንትራት አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ምትኬ አሰፋ በበኩላቸው ፕሮጀክቶቹ በተቀመጠላቸው ጊዜና የጥራት ደረጃ ተጠናቀው ለሕብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ተገቢው እንደሚፈፀም ገልፀዋል።
በውል ስምምነቱ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ምክትል ስራ አስኪያጅና የመስኖ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ገረመው ጀባኖ ከቢሮውና ኮንስትራክሽን ድርጅቱ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል ።
የተካሄደውን የውል ስምምነት ተከትሎ የቦታ/ሳይት ርክክብ በዛሬው እለት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል ።
See less
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 