በክረምት የበጎ አድራጎት ፈቃድ የተገነቡ ቤቶች ለወጣቱ የስራ እድልን ከመፍጠር ባሻገር ምቹና ተስማሚ የመኖሪያ አካባቢ ለማድረግ የላቀ ድርሻ ይኖረዋል። "አቶ ዳዊት ኃይሉ የክልሉ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ"
መስከረም 15/2019 (ወልቂጤ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በየም ዞን ደሪ ሳጃ ዙሪያ ወረዳ ድጋፍ ለሚሹ ሁለት መስማትና መናገር ለተሳናቸው ቤተሰቦች ያስገነባውን መኖሪያ ቤት በማጠናቀቅ የቁልፍ ርክክብ አድርጓል።
በርክክብ መርሃ ግብሩ በመገኘት የቁልፍ ማስረከቡን ያካሄዱት የክልሉ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ በክረምት የበጎ አድራጎት ፈቃድ የተገነቡ ቤቶች ለወጣቱ የስራ እድልን ከመፍጠር ባሻገር የአካባቢውን ገፅታ የሚቀይር ለኑሮ ምቹና ተስማሚ በማድረግ ረገድ የላቀ ድርሻ ስለሚኖረው የተጀመረውን የግንባታ አሰራር የራስን አቅም በመጠቀም፣ ህዝቡን እና የግል ባለሀብቱን በማሳተፍና በማስተባበር ማስቀጠል ይገባል ብለዋል ።
በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነትና አፍላቂነት የተጀመሩ እንዲሁም በክልሉ መንግሥት አመራር ሰጪነት የቀጠሉት የበጎ አድራጎት ሥራዎች በየም ዞን ደሪ ሳጃ ዙሪያ ወረዳ የአቅመ-ደካማ ወገኖች ቤት ግንባታ ስራ በስኬት በማጠናቀቅ ርክክብ ተደርጓል።
ቢሮው ከተሰጠው ተልዕኮ አኳያ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን በማሳደግ እና በሌሎች የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል አቶ ዳዊት ተናግረዋል። በዚህ የግንባታ ሂደት ከክልል እስከ ወረዳ ለተሳተፉ አካላት የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።
የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽመልስ እጅጉ ለሰው ልጆች ትልቁ መሰረት የሆነው የመኖሪያ ቤት ግንባታ በአካባቢው ለሚገኙ አቅመ ደካማ ወገን ቤተሰቦች በጥራትና በፍጥነት መገንባቱ የወጣቱ የስራ ላይ ሽግግር ማሳያ በመሆኑ ብዙሃኑን ተጠቃሚ የሚያደርጉ አሰራሮችን በማስፋት በቀጣይነት እንደሚንቀሳቀሱ አስታውቀዋል።
ከቤት ግንባታው ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ሰፊ ክትትልና ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ የቢሮው የስራ ሃላፊዎችና የማኔጅመንት አባላት አቶ ሽመልስ በዞኑ መንግስትና ህዝብ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የደሪ ሳጃ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደመላሽ ንጉሴ በበኩላቸው በወረዳው ደሪ ከተማ የተገነባው የሁለት የአቅመ ደካማ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት የመንግስትና የተቋሞቻችን ሕዝባዊ ወገንተኝነትን በተግባር ከማሳየትም አልፎ በማህበረሰቡ መካከል ያለውን የመረዳዳት ሂደትን ያጠናክራል ብለዋል።
የቤት ርክክብ የተደረገላቸው አቶ ግዛቸው ኢማም እና አቶ አዳሙ ኢማም በሰጡት አስተያየት ከዚህ ቀደም በወደቀ ቤት ውስጥ እየኖሩ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠው እንደነበር ገልጸው የክልሉ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ላደረገላቸው የመኖሪያ ቤት ግንባታና የቤት ቁሳቁስ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በመርሃ ግብሩ የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽመልስ እጅጉ ፣ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ አቶ ሀይሌ ደዊ፣ የደሪ ሳጃ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደመላሽ ንጉሴ፣ የቢሮው ማኔጅመንት አባላት ፣የየም ዞን ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ነገዎ ፣የዞንና የወረዳ ስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች እና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል ።
See less
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 