Skip to main content

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት ክቡር አቶ ማቴዎስ ሎምበሶ የሥራ ርክክብ አደረጉ።

መስከረም 26/2019 ዓ.ም (ወልቂጤ)

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት ክቡር አቶ ማቴዎስ ሎምበሶ ከቀድሞ የቢሮው ኃላፊ ከነበሩት አቶ ዳዊት ኃይሉ ጋር የሥራ ርክክብ አድርገዋል።

የውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ሎምበሶ በስራ ርክክብ ወቅት እንደገለጹት አቶ አቶ ዳዊት ኃይሉ በቢሮው ኃላፊነት በነበሩበት ወቅት ላበረከቱት አገልግሎትና ላከናወኑት የሥራ አፈጻጸም አድናቆታቸውን ገልፀው በቀጣይ የሥራ ዘመናቸውም ስኬትን ተመኝተዋል።

በክልሉ እያደገ የመጣውን የማህበረሰቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ ፍላጎት ለማማሟላት እና በማዕድንና ኢነርጂ ዘርፍ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት በየደረጃው ከሚገኙ የስራ ሃላፊዎች ፣ ባለሙያዎች ፣ አጋር አካላት እና ህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት በቀጣይነት እንደሚሰራ ገልፀው ለተደረገላቸው አቀባበልና ለተሰጣቸው ማብራሪያ ምስጋና አቅርበዋል።

የቀድሞው የቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ዳዊት ኃይሉ እንደገለፁት ባለፉት ዓመታት በቢሮ የተጀመሩና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደረጉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ቢሮው ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመሰራቱ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልፀው በቀጣይነትም ከቢሮው ጎን በመሆን የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

አዲሱ የቢሮ ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ሎምበሶ በመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ስራ ላይ ያላቸውን ልምድ መንግስት ካስቀመጠው ስትራቴጂ ጋር በማዋሃድ የተሻለ ውጤት እንደሚያስመዘግቡ በመተማመን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድና የቀጣይ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ቀርቧል።

የቢሮ ኃላፊ አቶ ማቲዮስ ሎምበሶ በአዲሱ ቢሮዋቸው መደበኛ የሥራ ኃላፊነታቸውንም ጀምረዋል።

በሥራ ርክክቡ ወቅት የቢሮው ምክትል ስራ ኃላፊዎች ፣ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ፣ የማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እና የቢሮው ማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል።

See less

Image