Skip to main content

የክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮና የተጠሪ ተቋም ማኔጅመንት አባላት በ100 ቀናት እቅድ አተገባበር ዙሪያ ተወያዩ ።

መስከረም 28/2019 (ወልቂጤ)

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ሎምበሶ፣ የቢሮውና የክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ባለስልጣን ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት በ100 ቀናት እቅድ አተገባበር ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።

የክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ሎምበሶ በቢሮውና በማዕድንና ኢነርጂ ባለስልጣን በቀጣይ ጊዜያት የሚፈፀመው የ100 ቀን እቅድ አተገባበር ከመደበኛው እቅድ የሚወሰድ ሆኖ የክልሉ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በቢሮውና በተጠሪ ተቋሙ በሚመለከታቸው የስራ ዘርፎች የጋራ በማድረግ ከጥቅምት ወር የመጀመሪያ ቀን አንስቶ በየደረጃው በተጠያቂነት ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል።

እቅዶቹ በዋናነት በተለያዩ ምክንያቶች የተጓተቱ ፕሮጀክቶችን ባጠረ ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ በሚያስችል መንገድ እንደሚተገበር የገለፁት አቶ ማቴዎስ የድጋፍ፣ የክትትልና የግምገማ ስርአትን ጠብቆ እንደሚመራ አመላክተዋል።

በተያያዘም ቢሮው ካስቀመጠው ግብ አኳያ በስር መዋቅሮች ላይ እየተተገበረ የሚገኘው አሰራር ለማጠናከርና መልካም ልምዶችን ለማስፋት ወቅቱን የጠበቀ ድጋፋዊ ክትትል ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በውይይቱ የተገኙት ማኔጅመንት አባላት በበኩላቸው የ100 ቀን እቅዱ በመንግስት ምስረታ ማግስት ተዘጋጅቶ ወደ ስራ እንዲገባ በክልሉ መንግስትና በቢሮው የተያዘው አካሄድ አመራሩና ሠራተኛው በተሻለ በፍጥነትና አቅም እንዲንቀሳቀሱ የሚያስችል መሆኑን ገልፀው ለእቅዱ ውጤታማነት የሚጠበቅባቸው እንደሚወጡ ተናግረዋል።

See less

Image