Skip to main content

ለመጠጥ ውሃና የሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች ግንባታ የሚደረገው ድጋፍ በተጠያቂነትና በባለቤትነት ሊመራ ይገባል።

"አቶ ማቴዎስ ሎምበሶ የክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ"

ጥቅምት 22/2019 (ወልቂጤ)

የክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ የስራ ሃላፊዎች በሀዲያ ዞን እየተገነቡ በሚገኙ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች ላይ ባካሄዱት የመስክ ምልከታ ጎልተው በወጡ ነጥቦችና ዙሪያ የዞንና የከተማ አስተዳደር ሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በሆሳዕና ከተማ ተወያይተዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኅላፊ አቶ ማቲዮስ ሎምበሶ በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች እየተገነቡ የሚገኙ የንፁህ መጠጥ ውሃና የሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች በወቅቱ ተጠናቀው ለማህብረሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡና በአሰራር ችግር ምክንያት እንዳይመክኑ በየደረጃው እየተደረገ የሚገኘውን ድጋፋ በየደረጃው በተጠያቂነትና በባለቤትነት ሊመራ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የሆሳዕና ከተማ የፍሳሽ ማጣሪያ/ሳኒቴሽን ፕሮጀክት በጥሩ አፈጻጸም ላይ እንደሚገኝ መመልከታቸውን የገለፁት አቶ ማቴዎስ በዞንና በከተማ ደረጃ የሚጠበቀውን የማቺንግ ፈንድ ክፍያ በአጭር ቀናት በመፈፀም በተያያዘው የስራ ግለት ፕሮጀክቱ እንዲጠናቀቅ መስራት ይገባል ብለዋል።

የጊምቢቾ ከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የገጠመውን ችግር ለመፍታት የመስክ ምልከታውን ተከትሎ ቢሮው፣ ዞኑ፣ ከተማ አስተዳደሩ እና ተቋራጭ ድርጅቱ በጋራ ያዘጋጁትን የአጭር ጊዜ እቅድ ተፈፃሚነቱን የመከታተልና የመደገፍ ስራ በአፅንኦት ማሳለጥ ይገባል ብለዋል።

የከተማ ውሃ አገልግሎቶችን አቅም በማሳደግ፣ የውሃ ተቋማት ብልሽት በሚያጋጥማቸው ወቅት በራስ አቅም በመገንባት፣ የውሃ ብክነትን በማስወገድ እና የውሃ መስመሮችን ከንክኪና ከጉዳት በፀዳ መንገድ እንዲሳለጡ በማድረግ አኳያ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አቶ ማቴዎስ ገልፀዋል።

በውይይቱ የተገኙት የቢሮው ምክትል የስራ ሃላፊዎች ወ/ሮ አለይካ ሽኩር ፣ ካሳዬ ተክሌ (ኢ/ር) እና የቢሮ አማካሪ አቶ ሃይሌ ደዊ በመስክ ምልከታው ባዩዋቸው ጥንካሬዎችና ጉድለቶች ዙሪያ አስተያየታቸውን ሰጥተው በጥናትና ዲዛይን ስራ፣ በተጠኑ ዶክመንቶች ክምችትና የመጠጥ ውሃ ተቋማትን ኦዲት በማድረግ ዙሪያ ከዞኑ ጀምሮ በሁሉም ስር መዋቅሮች የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

የሀዲያ ዞን ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ መለስ ሃይሌ የዞኑን ሕብረተሰብ በንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግና የውሃ ሽፋንን ለማሳደግ በመንግስት፣ በአጋር አካላትና በህብረተሰቡ ተሳትፎ ዘርፈ ብዙ ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው የክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ያደረገውን የመስክ ምልከታ ተከትሎ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እና ውስንነቶችን ለማረም ከሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎችና ባለድርሻዎች ጋር በመነጋገር እንደሚንቀሳቀሱ ገልፀዋል።

የሆሳዕና ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ስራ አስኪያጅ ደረጀ ኪዳኔ (ኢ/ር) በበኩላቸው በከተማው እየተካሄዱ በሚገኙ ሃገራዊና ክልላዊ ሁነቶች መነሻነትና የከተማውን ዕድገት ተከትሎ እየጨመረ የመጣውን የንፁህ ውሃ ፍላጎት ለማሟላት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው በቀጣይነትም የህብረተሰቡን እና የመንግስትን አቅም በማቀናጀት የተጀመረው የማስፋፍያ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

See less

Image