Skip to main content

የጊምቢቾ ከተማ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ቀሪ ተግባራት ለማፋጠን ህብረተሰቡን ያሳተፈ ስራዎች ላይ በትኩረት ማከናወን እንደሚገባ የቢሮ ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ሎምበሶ ገለፁ ።

ጥቅምት 21/2019 (ወልቂጤ)

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሀ ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ የስራ ሀላፊዎች፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሩ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በሀዲያ ዞን የጊምቢቾ ከተማ አስተዳደር የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ የሚገኙበትን ደረጃ ተዘዋውረው ተመልክተዋል ።

የክልሉ ውሀ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኅላፊ አቶ ማቲዮስ ሎምበሶ ቀደም ሲል በአለም ባንክ ፕሮጀክት ተጀምሮ የተለያዩ ምክንያቶች ስራውና ውሉ የተቋረጠው የጊምቢቾ ከተማ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ የክልሉ መንግስት ፕሮጀክቶችን ለማስፈፀም ካለው ቁርጠኝነት መነሻነት በክልሉ ዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈፀሚያ (SDG) በማስደገፍ በመንግስት የልማት ድርጅት ጋር በተገባው ውለታ መሰረት አሁናዊ የሚገኝበት አፈፃፀምና ያጋጠሙ ችግሮች በመስኩ መለየቱን ተናግረዋል።

የፕሮጀክቱ አፈፃፀም በአካባቢው እየተካሄደ ባለው የመሰረተ ልማት ዝርጋታና ተያያዥ ነጥቦች አማካይነት የግንባታ ስራው በሚፈለገው ፍጥነት እየሄደ አለመሆኑን የተመለከቱት አቶ ማቲዮስ ችግሮቹን በዘላቂነት በመፍታት ባጠረ ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ እንዲገባ ህብረተሰቡን ያሳተፈ ስራዎች ላይ በትኩረት ማከናወን እንደሚገባ አስታውቀዋል። ።

በቢሮ ኅላፊ ማዕረግ የክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ አለይካ ሽኩር የውሀ ግንባታው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ የከተማውን ህብረተሰብ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ በከተማው ፣ በዞኑና በከተማው የተጀመሩ ቅንጅታዊ ስራዎችን በማጠናከር ያልተቆራረጠ ድጋፋዊ ክትትል ማድረግ ይገባል ብለዋል ።

የቢሮው ምክትል ሃላፊና የመጠጥ ዉሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሃላፊ ካሳዬ ተክሌ (ኢ/ር) በበኩላቸው የፕሮጀክቱ ቀሪ ተግባራትን በታለመለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት መንቀሳቀስ እንደሚገባ አመላክተዋል።

በመጨረሻም ቀሪ ስራዎችን ባጠረ ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ በሚያስችሉ ነጥቦች ከክልሉ ውሀ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ፣ ከዞን ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ፣ ከከተማው አስተዳደር ፣ ከከተማው ውሃ አገልግሎት ፣ከተቋራጭ ድርጅቱ እና የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት የጋራ ውይይት መደረጉን ገልፀው አፈፃፀሙን የሚደግፍና የሚከታተል ቲም ተደራጅቶ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል።

በምልከታው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዉሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ አማካሪ አቶ ሃይሌ ደዊ፣ የሃዲያ ዞን ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ መለስ አ

ሀይሌ፣ የሆሳዕና ከተማ ውሃ፣ አገልግሎት ድርጅት ስራ አስኪያጅ ደረጀ ኪዳኔ (ኢ/ር) የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ አየለ ገዴ፣ሌሎች የቢሮው፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሩ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል ።

See less

Image