በክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኅላፊ አቶ ማቲዮስ ሎምበሶ የተመራ ልዑክ የሆሳዕና ከተማ የፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጀክት ምልከታ አደረገ።
ጥቅምት 21/2019 (ወልቂጤ)
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ሎምበሶ፣ የቢሮው የስራ ሃላፊዎች፣ የዞን፣ የከተማ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች እና የሚመለከታቸው አካላት በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር በመገንባት ላይ የሚገኘውን የፍሳሽ ማጣሪያ/ሳንቴሽን ፕሮጀክት የስራ ሂደት አስመልክቶ ምልከታ አድርገዋል።
የክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ሎምበሶ በመስክ ምልከታው ወቅት በሆሳዕና ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የፍሳሽ ማጣሪያ/የሳኒቴሽን ፕሮጀክት ለከተማው ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ በሚያስችል መንገድ በጥሩ ሁኔታ በመገንባት ላይ ይገኛል ብለዋል።
ፕሮጀክት ተጠናቆ ወደ ተግባር ሲገባ ለህብረተሰቡ ከሚሰጠው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አኳያ ወሳኝ በመሆኑ የውል ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት ቀሪ ስራዎች ከሚመለከታቸው ጋር በመነጋገር መስራት እንደሚጠበቅ አመላክተዋል።
የመስክ ምልከታው አላማ በክልሉ በተለያዩ ከተሞች እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶቹ በፍጥነትና በጥራት እንዲጠናቀቁ የክልሉ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ ቢሮው የመስክ ምልከታ ከማድረግ ባሻገር በፕሮጀክቶቹ ላይ የገጠሙ ማነቆዎች በመለየትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት ለችግሮቹ መፍቻ መንገዶችን ለማመላከት ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
ከጣሊያን መንግስት በተገኘው የገንዘብ ብድር እየተገነባ የሚገኘው የሆሳዕና ከተማ የፍሳሽ ማጣሪያና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት አሁናዋ አፈፃፀሙ 90.5% መድረሱ ሲገለፅ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ከተማዋን ፅዱ ለማድረግና ሁለቱንም የቆሻሻ አይነቶች በዘመናዊ መንገድ በማስወገድ እንዲሁም ከተማዋን ለነዋሪዎች የበለጠ ምቹና ተወዳዳሪ ለማድረግ የማይተካ ሚና እንደሚኖረው ተመላክቷል።
በመስክ ምልከታው የክልሉ ውሀ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ የስራ ሃላፊዎች፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሩ የሚመለከታቸው አመራሮችና ሌሌች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ።
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 