ARIA በክልሉ የገጠር ተራራማ አካባቢዎች ያካሄደው የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የአዋጭነት ጥናት ሰነድ ላይ ውይይት ተካሄደ።
ህዳር 2/2019 (ወልቂጤ)
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከምባታ ዞን ሀደሮ ጡንጦ ዙሪያና ቃጫ ቢራ ወረዳዎች እና ጠምባሮ ልዩ ወረዳ በገጠር ተራራማ አካባቢዎች ላይ በ ARIA የተጠና የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የጥናት ሰነድ የቢሮው ምክትል ኃላፊ ካሳዬ ተክሌ (ኢ/ር)፣ የሚመለከታቸው ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች፣ የጥናቱ አስተባባሪዎች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች በተገኙበት በቢሮው ጽህፈት ቤት ግምገማ ነክ ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ዘርፍ ኃላፊ ካሳዬ ተክሌ (ኢ/ር) የቀረበው የጥናት ሰነድ የተቋማት አስተዳደር ስርዓት ላይ ቢሮው የጀመራቸውን ተግባራት እንደሚያጠናክር ገልፀው በመደጋገፍ ላይ የተመሰረተ ውጤት ለማስመዝገብ ያግዛል ብለዋል።
ከግንባታ ስራ ባሻገር የመረጃ ልውውጥ እና የአሰራር ግልፀኝነት ተዋረዱን ጠብቆ
መካሄዱ ለመጠጥ ውሃ ተቋማት ዘለቄታዊነትና በባለቤትነት ሃላፊነትን በማሸጋገር ዙሪያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት (ኢ/ር) ካሳዬ ተናግረዋል።
የጥናት ሰነዱ ላይ የተመላከቱ ይዘቶች የትግበራ ሂደት ለማሳካት ከአጋር ድርጅቱ እና ከታችኛው መዋቅሮች ጋር በጋራ በመቀናጀት እንደሚንቀሳቀሱ ገልፀዋል።
የህብረተሰቡን የመጠጥ ውሃ ፍላጎት ለማሟላት በመንግስት ደረጃ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ኢ/ር ድርጅቱ በክልሉ የጀመራቸውን ፕሮግራሞች በቀጣይነትም አጠናክሮ እንዲያስቀጥል አመላክተዋል።
የፕሮሲድ ፕሮግራም አስተባባሪ አካሉ ካሳ (ኢ/ር) በበኩላቸው ፕሮግራሙ የገጠር ንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን ከግንባታ ባሻገር በማህበረሰቡ ባለቤትነት፣ በጠንካራ የጥገና አቅም እና ዘሌቄታዊ አገልግሎት እንዲኖራቸው የሚያስችል አጠቃላይ የትግበራ
ማዕቀፍ መሆኑን ገልፀዋል።
በክልሉ ከምባታ ዞን እና ጠምባሮ ልዩ ወረዳ በተመረጡ የገጠር ተራራማ ቀበሌያት የተጠናው የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ጥናት ችግር ፈቺና ውጤታማ በሆነ መንገድ መካሄዱን ተመላክቷል።
የጥናቱን ውጤት ወደ ትግበራ የማስገባት፣ ውጤቱን የማስፋፋት እና የይሁንታ ሂደት ላይ በመድረኩ የተገኙ አካላት በመወያየት የጋራ ።
ፕሮጀክቱ በፈረንሳይ መንግሥት ድጋፍ በ"IAF" እና "RCBDIA"ጥምረት "ፕሮሲድ" (PROCEED) በተባለ ፕሮግራም አማካኝነት የተካሄደ መሆኑ ተመላክቷል።
በመጨረሻም ለጥገና ምቹ የሆነ የውሃ ተቋማት ዲዛይንና ግንባታ ሂደት ላይ ለቢሮ መሃንዲሶችና ሀይድሮጂኦሎጂስቶች የፅንሰ ሃሳብ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል።
See less
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 