Skip to main content

በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በመገንባት ላይ የሚገኙ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች አፈፃፃም ቀርቦ ተገመገመ።

ህዳር 8/2019 (ወልቂጤ)

በፕሮጀክቶች የግንባታ ሂደት ላይ የክልሉ መንግስት በሰጠው ልዩ ትኩረት መነሻነት በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በመገንባት ላይ የሚገኙ ነባርና አዲስ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች አፈፃፀማቸውን ለማሻሻልና በግንባታ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት በሚል የቢሮው የስራ ሃላፊዎችና ከፍተኛ ባለሙያዎች በየደረጃው ከሚገኙ አካላት ጋር በመቀናጀት ባለፉት ጊዜያት የመስክ ምልከታና ድጋፋዊ ክትትል በማካሄድ እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ተመላክቷል።

በዚህም መሰረት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በመገንባት ላይ ከሚገኙ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች መካከል በዛሬው ዕለት የአስር የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ወቅታዊ የግንባታና ፋይናንሻል አፈፃፀማቸው እና የሚገኙበት ደረጃ አስመልክቶ የቢሮው ምክትል ኃላፊ ካሳዬ ተክሌ (ኢ/ር) ፣ የውሃ ስራ ተቋራጭ ድርጅቶች ስራ አስኪያጆችና የሚመለከታቸው ከፍተኛ ባለሙያዎች በተገኙበት በቢሮው ጽህፈት ቤት ግምገማ ነክ ውይይት ተካሄዷል።

መድረኩን የመሩት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሳኒቴሽን ዘርፍ ኃላፊ ካሳዬ ተክሌ (ኢ/ር) እንደተናገሩት ፕሮጀክቶች የውላቸውን ጊዜ ጠብቀው እንዲጠናቀቁና ወቅቱን የጠበቀ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል እያንዳንዱን የውሃ ተቋራጭ በኮንትራት የአስተዳደር ስርዓትን በጠበቀ መንገድ በመከታተል የግንኙነት ሂደቱ ተጠያቂነትን መሰረት አድርጎ መንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል።

የግንባታ አፈፃፀማቸው በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ አንዳንድ ፕሮጀክቶችንና በመድረኩ ጎልተው የወጡ ውስንነቶችን የሚመለከታቸው ተቋራጮች ወስደው የእርምት ስራ እንዲያከናውኑ ያሳሰቡት (ኢ/ር) ካሳዬ የተሻለ አፈፃፀም እያስመዘገቡ የሚገኙ ተቋራጭ ድርጅቶችን ለሕዝቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ቅድሚያ በመስጠት ቢሮው አሰራሩን በጠበቀ ሁኔታ በመገምገም በቀጣይነት እያሳተፈና እየደገፈ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

አንድን የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ጀምሮ ለማጠናቀቅ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ የሚባክን ሀብትና የስራ ጊዜ እንዳይኖር በጥንቃቄ መምራት እንደሚገባ አመላክተዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የቢሮው ከፍተኛ ባለሙያዎች እንደገለፁት ለፕሮጀክቶች የግንባታ ደረጃና ጥራት መሻሻል የፕሮጀክት ማናጀር ተሳትፎ የጎላ መሆኑን ጠቁመው በየደረጃው በተጠያቂነት ላንቀሳቀሱ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ፕሮጀክቶቹን ገንብተው ለማጠናቀቅ ውል የገቡ በመድረኩ የተገኙ የመጠጥ ውሃ ስራ ተቋራጭ ስራ አስኪያጆች የፕሮጀክቶቹን የግንባታና ፋይናንሻል አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበው ውይይት የተደረገበት ሲሆን ቢሮው የጀመረው ድጋዊ ድጋፋዊ ክትትል በየደረጃው ባሉ መዋቅሮችም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠቁመዋል።

See less

Image