Skip to main content

ጌታ ወረዳ ፉቻሬ 44 ቀበሌ ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውሃ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ህዳር 3/2019 ዓ.ም (ወልቂጤ)

በጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳ ፉቻሬ 44 ቀበሌ በመንግስት፣ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እምድብር ሀገረ ስብከትና በማህበረሰቡ ትብብር ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ከ8ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል።

ንጹህ የመጠጥ ውሃ ግንባታው 10 ቦኖዎች ተዘርግቶለት ለቀበሌውና በዙሪያው ላሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ተደራሽ እንደሚሆንም ተመላክቷል።

የፍቻሬ የንጹህ መጠጥ ውሃ ግንባታ ፕሮጀክት በሰከንድ ከ7 ሊትር በላይ ውሃ ያመርታል።

90 ኪሎ ዋት ማመንጨት የሚችል ሶላር ሲስተም የተገጠመለት ይህ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንደሚደረግም ተገልጿል።

በምርቃቱ የጉራጌ ዞን አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ አበራ ወንድሙ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ ማዕድንና ኤነርጂ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሳንቴሽን ዘርፍ ኃላፊ ኢንጅነር ካሳዬ ተክሌ፣ የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊና ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ደሳለኝ ፈቀደ፣ የዞንና የወረዳው ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ በጉራጌ ዞን በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የእምድብር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሉቃስ ፍቅሬ፣ ሌሎች የሀገረ ስብከቱ የስራ ሀላፊዎችና የአካባቢው ማህበረሰብ ተገኝተዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

See less

Image