ከ6ሚለየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የዘመናዊ ዲፈረንሺያል ጂፒኤስ መሳሪያ የግዢ ውል ስምምነት ተካሂዷል።
ከ6ሚለየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የዘመናዊ ዲፈረንሺያል ጂፒኤስ መሳሪያ የግዢ ውል ስምምነት ተካሂዷል።
የካቲት 8/2017ዓ.ም/ወልቂጤ/
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የውሃ፣መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ከአልጎሪዝም የንግድ ስራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር የዘመናዊ ዲፈረንሺያል ጂፒኤስ/Deferential GGPS/ መሳሪያ የግዢ ውል ስምምነት ተፈራርመዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የውሃ፣መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ ተወካይ ወ/ሮ አላይካ ሽኩር በውል ሰምምነቱ ወቅት እንደገለፁት እንደ ቢሮ ለመጠጥ ውሃ ጥናትና ዲዛይን ስራ አጋዥ የሆነ የዘመናዊ ዲፈረንሺያል ጂፒኤስ መሳሪያ የግዢ ውል ከአልጎሪዝም የንግድ ስራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር በ6ሚሊዮን 9መቶ78ሺህ ብር ቢሮው መፈራረሙን ገልፀዋል።
የቢሮ ኃላፊ ተወካይ ወ/ሮ አላይካ ሽኩር በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በከፍተኛ ወጪ የተቆፈሩ ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች ጥናትና ዲዛይን ስራ በተሻለ ጥራት ለማጥናት መሳሪያው ትልቅ እገዛ እንዳለው ተናግረዋል።በክልሉ ለሚሰሩ የመጠጥ ውሃ ዲዛይን ስራን መናዊ ዲፈረንሺያል ጂፒኤስ በመታገዝ የቢሮ የጥናትና ዲዛይን ስራ ደረጃን ከፍ እንዲል ያስችለዋል ብለዋል።በዉል ስምምነቱ የቢሮ ምክትልና የዘርፍ ኃላፊዎች፤ የቢሮ የማኔጅመንት አባላት እና የአልጎሪዝም የንግድ ስራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ-አስኪያጅ ተወካይ ወ/ሮ ሠላማዊት ወልደ ማሪያም ተገኝተዋል።
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 