Skip to main content

የህዝቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በግንባታ ላይ የሚገኙ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት በማጠናቀቅ በዘርፉ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ በቅንጅት እየተሠራ ነው:: የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ

የህዝቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በግንባታ ላይ የሚገኙ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት በማጠናቀቅ በዘርፉ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ በቅንጅት እየተሠራ ነው:: የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል  ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ 

የካቲት 28/2017(ወልቂጤ) 

የህዝቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በግንባታ ላይ የሚገኙ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት በማጠናቀቅ በዘርፉ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ  በቅንጅት እየተሠ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል  ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ ገለፁ። የክልል የውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት  የመጀመሪያ ስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ከተጠሪ ተቋማት፣  ከዞንና ልዩ ወረዳዎች እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቡታጅራ ከተማ የግምገማ መድረክ እያካሄደ ይገኛል። የክልሉ ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንደገለፁት በውሃ፣ በመስኖ፣ በማዕድንና ኢነርጂ ዘርፎች በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ዕቅድ በየደረጃው ከሚገኙ  ፈፃሚ አካላት ጋር ግልፀኝነት በመፍጠር ወደ ስራ መገባቱን አውስተው ይህንን ለማሳካት በውስን የሰው ሀይልና በጀት በመቀናጀትና በመደጋገፍ ርብርብ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል። በዚህም የህዝቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ ለማቅረብ በግንባታ ሂደት ውስጥ የሚገኙ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት በማጠናቀቅ በዘርፉ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ  በቅንጅት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል። በክልሉ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የመስኖ አውታር ልማት ግንባታና ተቋማት አስተዳደር ሚናው የላቀ በመሆኑ ትኩረት መሰጠቱን ነው በንግግራቸው ያመላከቱት። በመድረኩ የተገኙ ፈፃሚ አካላት በአፈፃፀም ወቅት የተገኙ መልካም ልምዶችን በማስፋት ጉድለቶችን በፍጥነት በማረም በቀሪ ጊዜያት ተልዕኮውን ለማሳካት መስራት ይጠበቅብናል ነው ያሉት። በግምገማ መድረኩ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር መሀመድ ኑርዬ ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የመሰረተ ልማት ልዩ አማካሪ አቶ መዝረዲን ሀሴን ፤ የክልሉ የውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ  የተጠሪ ተቋማት ሀላፊዎች፣ የቢሮው ምክትል የስራ ሀላፊዎች እና የዞን እንዲሁም የልዩ ወረዳዎች ሀላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

Image