Skip to main content

የዘመናዊ የጂኦ ፊዚካል መሳሪያ የግዢ ውል ስምምነት ተካሂዷል።

የዘመናዊ የጂኦ ፊዚካል መሳሪያ የግዢ ውል ስምምነት ተካሂዷል።

የካቲት 26/2017ዓ.ም/ወልቂጤ/

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የውሃ፣መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ከፐልስ/ pulse/ጠቅላላ የንግድ ስራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር የዘመናዊ የጂኦ ፊዚካል መሳሪያ የግዢ ውል ስምምነት ተፈራርመዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የውሃ፣መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ በውል ሰምምነቱ ወቅት እንደገለፁት ለመጠጥ ውሃ ጥናትና ዲዛይን ስራ አጋዥ የሆኑ የዘመናዊ የጂኦ ፊዚካል መሳሪያ የግዢ ውል ከፐልስ/ pulse/ጠቅላላ የንግድ ስራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር በ2 ሚሊዮን 636ሺህ ብር ቢሮው መፈራረሙን ገልፀዋል።

አቶ ዳዊት አክለውም በክልሉ በአንዳንድ አካባቢዎች በከፍተኛ ወጪ የተቆፈሩ ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች ከተቆፈረ በኃላ አልፎ አልፎ የመምከን ክስተት አየተፈጠረ መሆኑንና ይህን ችግር ለመቅረፍ መሳሪያው ትልቅ እገዛ እንዳለው ተናግረዋል።በክልሉ የሚሰሩ የመጠጥ ውሃ ዲዛይን ስራን በዘመናዊ ጂኦ ፊዚካል መሳሪያ በመታገዝ የመንግስት ውሰን ሀብት ሳይባክን ለታለመለት አገልግሎት እንዲውል ያስቻላል ብለዋል።በዉል ስምምነቱ የቢሮ ምክትልና የዘርፍ የስራ ኃላፊዎች፤የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር፣የመጠጥ ውሃ ጥናት እና ዲዛይን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንዲሁም ከፐልስ / pulse/ጠቅላላ የንግድ ስራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ-አስኪያጅ ተወካይ አቶ ሱራፌል ጌታቸው ተገኝተዋል።

Image