Skip to main content

በስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ

በስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም  አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ 

የካቲት 13/2017ዓ.ም 

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2017ዓ.ም በጀት ዓመት የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸምን ከክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮዎችና ከሚመለከታቸው  አካላት ጋር ገምግሟል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር  ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በግምገማ መድረኩ  መጀመሪያ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። ክቡር ሚኒስትሩ በንግግራቸው 2017ዓ.ም የበጀት ዓመት   በስድስት ወራት እቅድ  አፈጻጸም በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፣በውሃ ሀብት አስተዳደር እና ፣በኢነርጅ ልማት ዘርፎች  የህብረተሰቡን ዘላቂ  ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ  አኳያ  በገጠርም በከተማም  አመርቂ  ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል። በትግበራ ወቅት አንዳንድ የተንጠባጠቡ ስራዎች መኖራቸውን የጠቀሱት ክቡር ሚኒስትሩ  እነዚህ ተግባራት አንድም በእቅዳችን መሠረት በሚገባ ባለመተግበራችን በሌላ መልኩ ደግሞ ከአቅም በላይ በሆኑ  ምክንያቶች ያልተተገበሩ ናቸው ብለዋል። መድረኩ  ምን አቀድን ፣ ምን ተገበርን፣ በቀጣይስ  የተሻለ ስራ እንዴት እንስራ የሚለውን በጋራ በስፋት በመወያየት ችግሮችን በመቅረፍ ፣ የተሻሉ ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል የህብረተሰቡን ዘላቂ ተጠቃሚነት  ለማረጋገጥ ወሳኝ ነውም  ብለዋል። በየክልሎቹ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችንም በውይይት በማዳበር የነበሩ ውስንነቶችን በመቅረፍ ፣ ተሞክሮ የሚሆኑ ጠንካራ አሰራሮችን ወደ የራሳችን ወስደን የተሻለ ስራ ለመስራትም ያግዛል ብለዋል። ለውጤቱ ከፌደራል ጀምሮ እከታችኛው መዋቅር ያሉ  የውሃና ኢነርጂ ተቋማት ፣ ባለድርሻና አጋር አካላት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እንዲሁም የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢዎችና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ላደረጉት  ድጋፍ  ክቡር ሚኒስትሩ ምስጋና ችረዋል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2017ዓ.ም የበጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በስትራቴጅክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ በአቶ አለሙ መንገሻ እንዲሁም በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የተሰማሩ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች (CSO) ያሉበት ደረጃ ሪፖርት ደግሞ  በአማካሪ አቶ አበራ እንደሻው ቀርበዋል። እንደ ተቋም የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸምም 93.73 በመቶ መሆኑ በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል። በቀረቡ ሪፖርቶችም ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ውሃን በጥራት፣ በፍጥነትና በዘላቂነት ተደራሽ ለማድረግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  እያደረገ ያለውን ከፍተኛ ድጋፍ አመስግነዋው እንደ ክልል ትኩረት እና ድጋፍ  ይሻሉ  ያሏቸውን  ጉዳዮችም ተሳታፊዎች  አንስተዋል። በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ዙሪያ የውይይት መድረኩን የመሩት ክቡር ዶ/ር አብርሃ አዱኛ  ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተውበታል። በመድረኩ የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢዎችና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የፕላን ሚኒስቴር ተወካይ፣ የክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊዎች ፣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስራ አስፈጻሚዎችና የተጠሪ ተቋማት ሀላፊዎች የተሳተፉ ሲሆን በነገው እለት በሁለቱ የውሃና ኢነርጂ ረቂቅ ፖሊሲዎች ዙሪያ ውይይት እንደሚካሄድ ታውቋል። ።፦ዘገባው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ነው።

Image