ቆሻሻ ሀብት ነው (Wealth to Waste) በሚል መሪ ቃል የከተሞች ፅዳት መርሀ ግብር አከናውነዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ደን፣ አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ እና የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት የውሃ፣መስኖና ማዓድን ልማት ቢሮ በጋራ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ቆሻሻ ሀብት ነው (Wealth to Waste) በሚል መሪ ቃል የከተሞች ፅዳት መርሀ ግብር አከናውነዋል።
ሃላባ፣ መጋቢት 13/2017
የፅዳት መርኃ ግብሩን መርሀ ግብሩንበይፋያስጀመሩት የክልሉ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አብረሃም መጫ እና የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት የውሃ፣መስኖና ማዓድን ልማት ቢሮ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የቢሮ ም/ኃላፊና የውሃ ሀብት አሰተዳደር ዘር ኃላፊ በጋራ በሰጡት መግለጫ አካባቢያቸንን ውብና ፅዱ ማራኪ በማድረግ ለኑሮ የተመቻቸና ቱሪስት ሳቢ ማድረግ አለብን ብለዋል።
ሀላፊዎቹ አክለውም የአካባቢ ቆሻሻ ክምችት ለጤና ጠንቅ ከመሆን አልፎ የአየር ሚዛናዊነትን በመዛባት የሚያስከትለውን ችግር ለመቅረፍ የፅዳትና ውበት ስራዎችን በተቀናጀ መልኩ መስራት እንደሚገባ አስረድተዋል።ቆሻሻ ሀብት ነው ያሉት ሀላፊዎቹ ቆሻሻን ሪሳይክል በማድረግ ወደ ኦርጋኒክ ማዳበሪያ በመቀየር ዳግም ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
የሀላባ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ ሃጂ ኑርዬ በመርሀ ግብሩ የተገኙ ሲሆንበዕለቱ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት የውሃ፣መስኖና ማዓድን ልማት ቢሮ ከደን አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ ጋር በመቀናጀትበፅዳት መርሀ ግብር ባሻገር በውሃ አካላት ብክለት ፣ብክነት ፣ በውሃ የመጠቀም ፈቃድ አሰጣጥ እንዳሁም የዉሃ ሀብት አሰተዳደር ፖሊሲ ትግበራ ፖሊሲ ዙሪያ የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ የስልጠና መድረክ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አካሂደዋል።
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 