የቢሮው ኃላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ በተገኙበት የችግኝ ተከላ መረሀ-ግብር ተካሄደ
cerwater
Fri, 08/08/2025 - 11:00
በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል በመካሄድ ላይ በሚገኘው የችግኝ ተከላ መርሃ- ግብር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ መስኖና ማዕድን ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ በተገኙበት በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ አምበሊ ቀበሌ የችግኝ ተከላ ተካሄዷል ።
የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ስኬታማና ውጤታማ እንዲሆን የተተኩሉ ችግኞች በባለቤትነት መንከባከብና መጠበቅ እንደሚገባ የቢሮው ኃላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ ተናግረዋል ።
ዘርፉ ለወጣቱ የስራ ዕድል ለመፍጠር ፣ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ፣ የአየር ንብረት መዛባት ለመከላከልና የውሀ ምንጮች እንዳይደርቁ ሚናው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል ።
በመርሃ ግብሩ ከክልል፣ ከዞንና ከወረዳ የተወጣጡ የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል ።
Image
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 