የቢሮ ሃላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ በሃዲያና ሀላባ ዞኖች በግንባታ ላይ የሚገኙ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን ተመለከቱ
cerwater
Sat, 08/09/2025 - 11:06
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ውሀ ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ በሀዲያ ዞን የሾኔ ከተማ አስተዳደር ፣ በሃላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በ1ኛ ጤፎ ቀበሌ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙትን የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ የመስክ ምልከታ አድርገዋል ።
የመስክ ምልከታውን ተከትሎ የፕሮጀክቶቹ ኮንትራክተሮች ፣ ከአማካሪ መሀንዲስና ሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በቀሪ ስራዎችና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል ።
ቀሪ ስራዎቹን በፍጥነት በማጠናቀቅ ለምርቃት ዝግጁ እንዲሆኑ የቢሮ ሃላፊው አቶ ዳዊት አሳስበዋል።
በምልከታው ከፌደራል፣ ከክልል፣ ከዞን፣ ከወረዳና ከከተማ አስተዳደር የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል ።
Image
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 