በክልሉ የሀይድሮጂኦሎጂና የከርሰ ምድር ውሃ ጥናት ስራ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገለፀ
የውሀ ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአለም ባንክ ባገኘው ድጋፍ ዘላቂ የሀይድሮጂኦሎጂና የከርሰ ምድር ውሃ ጥናት ለማካሄድ ከአማካሪ ድርጅቶች ጋር ያደረገውን ውል ስምምነት ተከትሎ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በላይኛው ብላቴ አካባቢ የተጀመሩ ቅድመ ጥናት ስራዎች በተቀናጀ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን ቢሮው አስታውቋል ።
የክልሉ ውሀ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ ተወካይና ምክትል ቢሮ ኃላፊ ፣ የመጠጥ ውሀ ሀብት ጥናትና ዲዛይን አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት ኢንጂነር አየለ ኬርጋ እንደገለፁት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በመካሄድ ላይ የሚገኘው የሀይድሮጂኦሎጂና የከርሰ ምድር ውሃ ጥናት ስራ በትክክለኛ መረጃ ተደግፎ በተያዘለት ጊዜ ሰሌዳ እንዲጠናቀቅ ቢሮውና ስር መዋቅሮች ለጥናቱ የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ።
የሀይድሮጂኦሎጂና የከርሰ ምድር ውሃ ጥናት ስራው የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በክልል ደረጃ የተጀመሩ ሥራዎችን የሚያጠናክር መሆኑን ገልፀዋል ።
በቢሮ ሀላፊ ማዕረግ የውሀ ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የውሀ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ አለይካ ሽኩር በበኩላቸው ጥናቱ ለቢሮው ተጨማሪ አቅም በመሆኑ ለጥናት ስራው አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች በቢሮው በኩል በበቂ መጠን ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል ።
የጥናት ስራውን በማከናውን ላይ ከሚገኙ ባለሙያዎች መካከል የኮርመር ማማከር አገልግሎት ተወካይ አቶ ወይሳ መሳይ እንደተናገሩት በክልሉ በተመረጡ ዘጠኝ ቀበሌያት የሀይድሮጂኦሎጂ ከርሰ ምድር ውሃ ጥናት ስራ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል ።
ጥናቱ ያስፈለገበትን ምክንያት ሲገልፁ የውሀ ጉድጓዶች ሲቆፈሩ አካባቢን ሳይበክሉና ሕዝብን ደህንነት በመጠበቅ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መንገድ ለማስቀጠል ያለመ መሆኑን ተናግረው በቢሮው በኩል ለጥናቱ መሳካት ተገቢው ድጋፍ በመደረግ ላይ ይገኛል ብለዋል ።
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 