Skip to main content

በዋን-ዋሽ እና ኮ-ዋሽ ፕሮግራሞች የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ አቅዶ እንደሚሰራ ቢሮው አስታወቀ ።

መስከረም 08/2018 ዓ.ም (ወልቂጤ)

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ውሀ ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ የኮ-ዋሽ እና የዋን ዋሽ ፕሮግራሞች ዓመታዊ የምክክር መድረክ አፈፃፀም የቢሮው ማኔጅመንት አባላት እና የፕሮግራሙ ባለሙያዎች በተገኙበት ተገመገመ።

የክልሉ ውሀ ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ እንደተናጉሩት በወራቤ ከተማ በተካሄደው ምክክር መድረክ ላይ በተሰጡ አስተያየቶችና በቀረቡ ጥያቄዎች መሰረት እንዲሁም የ2017 የኮ-ዋሽ እና የዋን ዋሽ እቅድ አፈጻጸምን መነሻ በማድረግ በየደረጃው የሚገኙ ፕሮጀክቶችን በተያዘው በጀት ዓመት ተጠናቀው የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የአጭርና በመካከለኛ ጊዜ ዕቅድ በማዘጋጀት እንደሚሰራ ገልፀዋል ።

የፕሮጀክቶቹን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ዘርፎችንና የስራ ክፍሎችን በማቀናጀት፣ መልካም አፈፃፀም የታየባቸውን ልምድ እንዲለዋወጡ ከማድረግ ባሻገር ቅንጅታዊ አሠራር በመዘርጋት እና የተጠናከረ ድጋፋዊ ክትትል በማድረግ የፕሮጀክት አፈፃፀም ከፍ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል።

በአንዳንድ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ የታዩ ጉድለቶችን በተለይ ከማቺንግ ፈንድ ማዋጣት ላይ ከሚመለከታቸው ጋር በመቀናጀት በአካል ወርዶ በማየት መፍትሄዎችን በማመላከት ወደ ውጤት እያሸጋገሩ መስራት እንደሚገባ አቶ ዳዊት ገልፀው።

በመድረኩ የተገኙት የቢሮው ምክትል ሀላፊዎች በቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በመድረኩ የተገኙ ተሳታፊዎች እንደገለጹት በፕሮግራሞቹ የተከናወኑ ፕሮጀክቶች በሙሉ አቅማቸው ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ መከታተልና መደገፍ እንደሚገባ እንዲሁም ውጤታማ ለማድረግ የተጀመረውን ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር መንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል።

መድረኩን ለማሳካት በየደረጃው የተደረገው ርብርብ አስተማሪና  በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተመላክቷል።

Image