Skip to main content

የከተሞች ውሀና ሳኒቴሽን ፌዴሬሽንና የውኃ አገልግሎቶች ማህበር የውኃ ተቋሟት አስተዳደር ላይ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ የቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ ገለፁ ።

መስከረም 14/2018 ዓ.ም (ወልቂጤ) 

የከተማውኃ አገልግሎቶች ውስጣዊ አሰራርን በማሻሻል ላይ መሰረት ያደረገ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የከተማ ውሀ አገልግሎቶች ማህበር 3ኛ ዙር ፎረም በወራቤ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል ። 

የማዕከላዊኢትዮጵያ ክልል ውኃ ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ በመድረኩ ተገኝተው እንደተናገሩት የከተሞች ውሀና ሳኒቴሽን ፌዴሬሽንና የውኅ አገልግሎቶች ማህበር የውኃ ተቋሟት አስተዳደር ላይ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል ። 

በክልላችንየከተሞች ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ የከተማውን ማህበረሰብ ፍላጎት የሚመጥን የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦትንና የሳኒቴሽን አገልግሎትን የሚያሳልጥ ስራ ሊከናወን ይገባል ብለዋል ። 

በተጠናቀቀውበጀት አመት ክልሉ ሶስት ከፍተኛ የውኅ ተቋሟት ግንባታን በማጠናቀቅ (ቡኢ፣ ዳሎቻና ሺንሺቾ) ማስመረቁን ያነሱት አቶ ዳዊት እነዚህና ሌሎች የውሀ ተቋሟት በራሳቸው ገቢ እንዲንቀሳቀሱ፣  ጥራት ያለውናየማይቋረጥ ውሀ ለህብረተሰቡ እንዲያቀርቡ መስራት ይገባል ብለዋል ።

በመጨረሻምየኢትዮጵያ ከተሞች ውኃና ሳኒቴሽን ፌዴሬሽን የውሀ አገልግሎቶች አጋርነትን፣ የክልሉን ውና ሳኒቴሽን ፌዴሬሽን በማጠናከር ፣ የውኅ አገልግሎቶች በቁሳቁስ ፣ በሰው ሃይል፣ በፋይናንስ እንዲጠናከሩ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲያስቀጥል ገልፀዋል ።

 

በመድረኩተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የወራቤ ከተማ ከንቲባ አቶ ያሲን ኸሊል በበኩላቸው የወራቤን ከተማ ንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ለማሻሻልና የውሀ ሽፋኑን ለማሳደግ የክልል፣ የዞንና የከተማው መዋቅሮች በመቀናጀት ሰፊ ተግባራት በማከናወን ላይ መሆኑን ተናግረዋል ። 

በተያያዘምየከተማዋን ዕድገት ለማፋጠን በኮሪደር ልማት ፣ በአስፓልት ግንባታና በሌሎች መሰረተ ልማቶች ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። 

‎በመድረኩላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ ፣ የቢሮው ምክትል ሃላፊዎችና የቢሮ ኃላፊ አማካሪ፣ የኢትዮጵያ ከተሞች የውኅና ሳኒቴሽን ፌደሬሽን ዋና ዳይሬክተር ፣የወራቤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፣

‎ የውኃናኢነርጂ ሚኒስተር የውሃ ዘርፍ መሪ ስራ አስፈፃሚ ፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስተር የሳኒቴሽን ዘርፍ መሪ ስራ አስፈጻሚ ፣የክልሉ ውሃ አገልግሎቶች ማህበር ሰብሳቢ አቶ ሰይድ አማን ፣‎ የአዳማ ውሃ አገልግሎት ስራ አስኪያጅና የፌደሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል ።

ለመድረኩየተዘጋጁ ሰነዶች በሚመለከታቸው አካላት በመቅረብ ላይ ይገኛል ።

Image