የከተሞች ውሀና ሳኒቴሽን ፌዴሬሽንና የውኃ አገልግሎቶች ማህበር የውኃ ተቋሟት አስተዳደር ላይ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ የቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ ገለፁ ።
መስከረም 14/2018 ዓ.ም (ወልቂጤ)
የከተማ ውኃ አገልግሎቶች ውስጣዊ አሰራርን በማሻሻል ላይ መሰረት ያደረገ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የከተማ ውሀ አገልግሎቶች ማህበር 3ኛ ዙር ፎረም በወራቤ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውኃ ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ በመድረኩ ተገኝተው እንደተናገሩት የከተሞች ውሀና ሳኒቴሽን ፌዴሬሽንና የውኅ አገልግሎቶች ማህበር የውኃ ተቋሟት አስተዳደር ላይ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል ።
በክልላችን የከተሞች ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ የከተማውን ማህበረሰብ ፍላጎት የሚመጥን የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦትንና የሳኒቴሽን አገልግሎትን የሚያሳልጥ ስራ ሊከናወን ይገባል ብለዋል ።
በተጠናቀቀው በጀት አመት ክልሉ ሶስት ከፍተኛ የውኅ ተቋሟት ግንባታን በማጠናቀቅ (ቡኢ፣ ዳሎቻና ሺንሺቾ) ማስመረቁን ያነሱት አቶ ዳዊት እነዚህና ሌሎች የውሀ ተቋሟት በራሳቸው ገቢ እንዲንቀሳቀሱ፣ ጥራት ያለውና የማይቋረጥ ውሀ ለህብረተሰቡ እንዲያቀርቡ መስራት ይገባል ብለዋል ።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ከተሞች ውኃና ሳኒቴሽን ፌዴሬሽን የውሀ አገልግሎቶች አጋርነትን፣ የክልሉን ውና ሳኒቴሽን ፌዴሬሽን በማጠናከር ፣ የውኅ አገልግሎቶች በቁሳቁስ ፣ በሰው ሃይል፣ በፋይናንስ እንዲጠናከሩ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲያስቀጥል ገልፀዋል ።
በመድረኩ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የወራቤ ከተማ ከንቲባ አቶ ያሲን ኸሊል በበኩላቸው የወራቤን ከተማ ንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ለማሻሻልና የውሀ ሽፋኑን ለማሳደግ የክልል፣ የዞንና የከተማው መዋቅሮች በመቀናጀት ሰፊ ተግባራት በማከናወን ላይ መሆኑን ተናግረዋል ።
በተያያዘም የከተማዋን ዕድገት ለማፋጠን በኮሪደር ልማት ፣ በአስፓልት ግንባታና በሌሎች መሰረተ ልማቶች ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
በመድረኩ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ ፣ የቢሮው ምክትል ሃላፊዎችና የቢሮ ኃላፊ አማካሪ፣ የኢትዮጵያ ከተሞች የውኅና ሳኒቴሽን ፌደሬሽን ዋና ዳይሬክተር ፣የወራቤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፣
የውኃና ኢነርጂ ሚኒስተር የውሃ ዘርፍ መሪ ስራ አስፈፃሚ ፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስተር የሳኒቴሽን ዘርፍ መሪ ስራ አስፈጻሚ ፣የክልሉ ውሃ አገልግሎቶች ማህበር ሰብሳቢ አቶ ሰይድ አማን ፣ የአዳማ ውሃ አገልግሎት ስራ አስኪያጅና የፌደሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል ።
ለመድረኩ የተዘጋጁ ሰነዶች በሚመለከታቸው አካላት በመቅረብ ላይ ይገኛል ።
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 