በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ233 ሚሊዮን ብር የዳጋግ ጉርዴ መስኖ ፕሮጀክት ሥራ ተጀመረ።
cerwater
Wed, 10/08/2025 - 14:38
ፕሮጀክቱ በክልሉ ግብርና ቢሮ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም የገንዘብ ድጋፍ የሚሰራ ሲሆን ሲጠናቀቅ ከ347 ሄክታር በላይ መሬት በማልማት በርካታ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል።
ፕሮጀግቱ ሲጠናቀቅ ግብርናን በማዘመን፣ ከዝናብ ጥገኝነት በመውጣት እና የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ለማረጋገጥ የጎላ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።
በ8 ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የተገለፀው ይህ ፕሮጀክት የበርካ ጊዜ የህዝብ ጥያቄ ሆኖ ስለመቆየቱ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ተናግረዋል።
በፕሮግራሙ የክልሉ መስኖ ተቋማት ልማት ኤጀንሲ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ካሳዬ ተክሌ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ መላኩ ባፋ፣ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ማናጀር አቶ ከድር መሀመድ እና ሌሎች በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
Image
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 