Skip to main content

በበጀት ዓመቱ አንደኛ ሩብ ዓመት በክልሉ 20 የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ከ164 ሺ በላይ ህብረተሰብ ተጠቃሚ ማድረጉን ቢሮው ገለፀ ።

መስከረም 30/2018 ዓ.ም (ወልቂጤ)

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሀ ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም የቢሮው አመራሮችና ማናጅመንት አባላት በተገኙበት ገመገመ ።

ቢሮው ከክልል መንግስት ፣ ከአጋር አካላትና ከፌደራል እየተደረገ ባለው ድጋፍ፣ በቢሮውና ስር መዋቅሮች የጋራ እንቅስቃሴ ያደሩና አዳዲስ የመጠጥ ውኃ ግንባታዎችን በተያዘው በጀት ዓመት በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የቢሮው ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ ገልፀዋል ።

በተያዘው በጀት ዓመት አንደኛ ሩብ ዓመት በአጠቃላይ 20 የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ በክልሉ ከ164 ሺ በላይ ህብረተሰብ አካላትን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን በሪፖርቱ ተመላክቷል ።

ለረጅም ጊዜ የተጓተቱና የመልካም አስተዳደር ችግር የነበሩ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ከሚመለከታቸው በመነጋገር ወደ ግንባታ እንዲገቡ ተደርጓል ።

የውኃ መገኛ የጥልቅ ጉድጓድ ጥናት በጂኢፊዝካል መሳሪያ የታገዘ የጥናት ስራ በገጠር እና በከተሞች  የመጠጥ ውኃ ጥናት ስራዎች መከናወን መቻሉ ተነስቷል ።

180 የገጠር መጠጥ ውኃ ማህበራትን ኦዲት በማድረግ 374,974 ብር ጉድለት ተመላሽ መደረጉንና የውሀ ተቋማት አስተዳደር ላይ በሩብ ዓመቱ አበረታች ስራዎች መከናወናቸው ታይቷል ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ በውይይቱ ማጠቃለያ እንደተናገሩት በክልሉ ሁሉም መዋቅሮች ላይ 
የተጀመሩ የመጠጥ ውኃ ግንባታ ስራዎች ላይ በየጊዜው ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝ ገልፀው በወቅቱ ያልተጠናቀቁ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ችግሮችን ባጠረ ጊዜ ተለይቶ አስፈላጊው ማስተካከያ ይደረጋል ብለዋል።

ከውሀ ቆጠራና ሽፋን ጋር ተያይዞ የተሰሩ ተግባራት መረጃ ተጠቃሎ ከሚመለከታቸው አካላት የጋራ መግባባት መፍጠርና ለቀጣይ ተልዕኮ ዝግጁ መሆን ይገባል ብለዋል ።

በየዘርፉ የተጀመሩ ቅንጅታዊ አሰራር የማጠናከር ፣ ሀብትን በቁጠባ የመጠቀም፣ የለውጥ ስራዎችን በቢሮው የማጠናከር ስራ እንደሚቀጥል አቶ ዳዊት ተናግረዋል ።

Image