Skip to main content

በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ የሳዳማ-ማሱዳ ቀበሌ የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተመረቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደረገ ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ሳዳማ ማሱዳ ቀበሌ የንፁህ መጠጥ ውኃ ግንባታ ተጠናቆ መመረቁንና ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት መስጠት መጀመር ችሏል ።

ካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ በተባለ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ገንዘብ ድጋፍ ፣ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የሆሳዕና ሀገረ ስብከት አስተባባሪነት ፣ በክልሉ ፣ በዞኑና በወረዳው ቅንጅታዊ እንቅስቃሴ ተገንብቶ የተጠናቀቀው የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተጠናቆ የቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ እና የሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል ።

የውሀ ፕሮጀክቶቱ ከ19 ኪሎ ሜትር በላይ የውሀ መስመር ዝርጋታ ተደርጎ በ18 የዉሀ ቦኖዎች ተደራሽ መሆኑንና ከ15 ሺ በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ አካላት አግልግሎቶት እንደሚሰጥ በምረቃው ወቅት ተገልፆአል ።

የውሀ ፕሮጀክቱን ሰርቶ ለማጠናቀቅ - $482,000 ዶላር ፈጅቷል ።

የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቱ በመጠናቀቁ ከዚህ ቀደም ለውኃ ወለድ በሽታ ተጋላጭ የነበሩ ነዋሪዎችን ጤና ከመጠበቅ ባሻገር ፣ ለንፁህ መጠጥ ውሀ ፍለጋ ይባክን የነበረ ጊዜ በመቆጠብ ለህፃናት፣ ለወጣቶችና እናቶች የተረጋጋ ማህበራዊ ክዋኔ ተሳትፎ የሚያጎለብት መሆኑን አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል ።

Image