Skip to main content

ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ባጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅና የማህበረሰቡ ተጠቃሚነትን ለማሻሻል እንደሚሰራ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሀ ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ አስታወቀ ።

ጥቅምት 11/2018 (ወልቂጤ)

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሀ ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ የ2018 በጀት አመት የአንደኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ የቢሮና ተጠሪ ተቋማት ማናጅመንት አካላት በተገኙበት ገመገመ ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሀ ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ በውይይት መድረኩ እንደተናገሩት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ የመጠጥ ውሃና የመስኖ ፕሮጀክቶች እንዲሁም በማዕድንና ኢነርጂ ዘርፍ የተጀመሩ ሥራዎችን ባጠረ ጊዜያት በማጠናቀቅ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል ብለዋል ።

ቢሮው በ1ኛ ሩብ ዓመት በመንግስት፣ በአጋር አካላት የበጀት ድጋፍና በህብረተሰብ ተሳትፎ 20 የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ከ164 ሺ በላይ ህዝብን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን በሪፖርቱ ተመላክቷል ።

በአረንጓዴ አየር ንብረት ፈንድ (GCF) ድጋፍ ከ33 ሺ በላይ ህብረተሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት እንዲጠናቀቅ ሰፊ ርብርብ ተደርጓል ተብሏል ።

180 የገጠር መጠጥ ውኃ ማህበራትን ኦዲት በማድረግ 374,974 ብር ጉድለት የተለየ ሲሆን ከማስመለስ ረገድ እና  የውሀ ተቋማት አስተዳደር በማጠናከር የሀብት ብክነት የመከላከል ሥራ በትኩረት መሠራት እንዳለበት ተመላክተዋል።

በመስኖ ዘርፍ በራስ ሀይልና በአማካሪ ጥናቶች ግንባታ ሂደት በጊዜያዊነትና በቋሚነት ለ5000 ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠሩን ተገልፆአል ።

በSDG በPACT በFSRP እና SHIDIP በጀት ድጋፍ አስር የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ ስራዎች ላይ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ።

በማዕድን ዘርፍ 1565 ወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚ ማድረግ ሲቻል ከ43 ሚሊየን ስድስት መቶ ሺ በላይ ገቢ ማሰባሰብ ተችሏል ።

በኢንዱስትሪ ማዕድናት ላይ በፑምስ፣ በፊልድስፓር እና በላይምስቶን 11,772 ቶን ማምረት ሲቻል በእነርጂው ዘርፍ 14,780 የሶላር ቴክኖሎጂ በማሰራጨት 73,900 ማህበረሰብን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ተገምግሟል ።

የውሀ ሀብት ቆጠራ ስራ መረጃን በተያዘው ወር የማጠናቀቅ ፣ የመስኖና የመጠጥ ውኃ ተቋማት አስተዳደር ማጠናከር፣ የገጠር ኮሪደር ስራዎች ላይ በኢነርጂው ዘርፍ የተጀመሩ ድጋፎችን ማስቀጠል፣ የፕሮጀክቶች ቁጥጥርና ክትትል ስራ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን አቶ ዳዊት ኃይሉ ተናግረዋል ።

በቢሮውና ተጠሪ ተቋማት መካከል የተጀመረው ቅንጅታዊ አሰራር ዘርፎቹን ውጤታማነ እያደረገ እንደሚገኝ የገለፁት ማናጅመንት አባላቱ መድረኩ በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንዳነሳሳቸው ተናግረዋል።

በመጨረሻም በተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ዙሪያ በቢሮ ኅላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ ፣በማድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ማኔዶ ፣ በመስኖ ተቋሟት ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ሃላፊ አቶ መሀመድ ስራጅ እና በቢሮው ምክትል ሃላፊዎች ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል ።

Image