ለረዥም ጊዜ የተጓተቱ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እና የማስፈፀም አቅም ለማሳደግ እንዲሁም ተቋማዊ አሰራር መሠረት ለማስያዝ ድጋፋዊ ክትትል በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የክልሉ ውሀ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ አስታወቀ ።
ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም (ወልቂጤ)
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ከተጠሪ ተቋሟት ጋር በመቀናጀት በ2018 የመጀመሪያ አራት ወራት እቅድ አፈጻጸም ላይ በክልሉ በሚገኙ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ድጋፋዊ ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛል ።
ድጋፋዊ ክትትሉን የቢሮውና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ማኔጅመንት አባላት በመካሄድ ላይ ሲገኙ በዞኖችና በልዩ ወረዳዎች በውሀ፣ በመስኖ እና በማዕድን ኢነርጁ ዘርፍ ያለውን የዝግጅት ምዕራፍ ፣ ያለፉት አራት ወራት የተግባር ምዕራፍ እና ልዩ ትኩረት በሚሹ የመጠጥ ውኃ፣ የመስኖ ተቋማት ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይና የማዕድንና ኢነርጂ ስራዎች የሚገኙበት ደረጃ አስመልክቶ ድጋፋዊ ክትትልና የመስክ ምልከታ እንደሚካሄድ የቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ ገልፀዋል ።
ድጋፋዊ ክትትሉ በዋነኛነት ለረዥም ጊዜ የተጓተቱ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እና የማስፈፀም አቅም ለማሳደግ እንዲሁም ተቋማዊ አሰራር መሠረት ለማስያዝ ድጋፋዊ ክትትሉ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን የቢሮው ኃላፊ ተናግረዋል ።
ድጋፋዊ ክትትሉን ተከትሎ በየዘርፉ የሚታዩ ጥንካሬዎችን የማስቀጠል ፣ በአፈፃፀም ደረጃ ጉድለት በሚስተዋልባቸው ስራዎች ላይ የመፍትሄ ሃሳቦች እንደሚሰጥባቸው እና አፈፃፀማቸውን የሚያሻሽል ግብረ መልስ ለሚመለከታቸው አካላት እንደሚሰጥ ይጠበቃል ።
በዛሬው ዕለት በምስራቅ ጉራጌ ዞን ፣ በስልጤ ዞንና በሀዲያ ዞን ውሀ ፣ ማዕድንና ኢነርጂ መዋቅሮች ድጋፋዊ ክትትል እየተደረገ ሲገኝ በቀጣይ በሌሎች መዋቅሮችም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ።
የድጋፋዊ ክትትል ሂደቱን በቀጣይ ተከታትለን እናቀርባለን ።
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 